Lyrics

ሲመሽ ሲመሽ ይከፋኛል ሲመሽ ሲመሽ ሲመሽ ቅር ይለኛል ሲመሽ የአንቺ ሆደ ባሻ የአንቺዉ አስታዋሽ አይ ብታይ ሲመሽ በምሽት ጨረቃ ጨረቃ ቢያጌጥም ሰማዩ እኔ ግን ቆሚያለሁ አይኖቼ እያዩ ሳያዩ በኮከብ ባማረዉ ባማረዉ በዚህ ልዩ ማታ አብረሽኝ ብትሆኚ ብትሆኚ ነበር የኔ ደስታ ማታ ማታ ማታ ማታ ባየሽኝ እንዴት እንደምሆን ናፍቀሽኝ ማታ ማታ ማታ ማታ ባየሽኝ እንዴት እንደምሆን ናፍቀሽኝ ሲመሽ ሲመሽ ይከፋኛል ሲመሽ ሲመሽ ሲመሽ ቅር ይለኛል ሲመሽ የአንቺ ሆደ ባሻ የአንቺዉ አስታዋሽ አይ ብታይ ሲመሽ ጀንበሯ ስትገባ ስትገባ ደርሶ ይጨንቀኛል በአለም ላይ ብቻዬን የቀረሁ ያህል ይሰማኛል በምሽት ከአንቺ ጋ ከአንቺ ጋ ያሳለፍኩት ደስታ ከሆዴ አልወጣ አለኝ ያ ጊዜ ያ ጣፋጭ ትዝታ ማታ ማታ ማታ ማታ ባየሽኝ እንዴት እንደምሆን ናፍቀሽኝ ማታ ማታ ማታ ማታ ባየሽኝ እንዴት እንደምሆን ናፍቀሽኝ ማታ ማታ ማታ ማታ ባየሽኝ እንዴት እንደምሆን ናፍቀሽኝ ማታ ማታ ማታ ማታ ባየሽኝ እንዴት እንደምሆን ናፍቀሽኝ
Writer(s): Tsehaye Yohannes Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out