Lyrics

ሰዉ ያስባል ሳትይ ምነዉ በዚያዉ ጠፋሽ ምነዉ በዚያዉ ጠፋሽ አንዴ ብቅ አልሽና ዉሃ ሆነ ሽታሽ ዉሃ ሆነ ሽታሽ በይሉኝታ አትጥፊ ቀኑ ቢገፋም ቤት ያፈራዉ ፍቅር መቼም ላንቺ አይጠፋም ሰዉ ያስባል ሳትይ ምነዉ በዚያዉ ጠፋሽ ምነዉ በዚያዉ ጠፋሽ አንዴ ብቅ አልሽና ዉሃ ሆነ ሽታሽ ዉሃ ሆነ ሽታሽ በይሉኝታ አትጥፊ ቀኑ ቢገፋም ቤት ያፈራዉ ፍቅር መቼም ላንቺ አይጠፋም ቀድሞም የሰዉ ነገር አንቺን ይከብድሻል ዛሬም በይሉኝታ ከኔ ጋ ርቀሻል ብዙም ባይጋነን ብዙ ባያኮራ አንቺን ለመቀበል ከጐጆዬ ጋራ ንፁህ ልቤን አስፍቼ ለመጪዉ ፍቅር ዘመን ዝግጁ ነኝ ምን ጊዜም አምኜሽ ለመታመን ብቻ ነይ እንጂ ብቻ ነይ እንጂ ቤት ያፈራዉን ፍቅር አልነፍግ እንዳንቺ ብቻ ነይ እንጂ ብቻ ነይ እንጂ ቤት ያፈራዉን ፍቅር አልነፍግ እንዳንቺ የለም እንዳልልሽ ተዘጋጅቻለዉ (ብቻ) ጓዳዉን ደጁንም አሳምሬዋለዉ (ብቻ) ምንም ጊዜዉ ቢርቅ ምንም ቀን ቢገፋም (ብቻ) ለአንቺ ሚሆን ፍቅርምን ጊዜም አይጠቁርም ብቻ ነይ እንጂ ብቻ ነይ እንጂ ቤት ያፈራዉን ፍቅር አልነፍግ እንዳንቺ ሰዉ ያስባል ሳትይ ምነዉ በዚያዉ ጠፋሽ ምነዉ በዚያዉ ጠፋሽ አንዴ ብቅ አልሽና ዉሃ ሆነ ሽታሽ ዉሃ ሆነ ሽታሽ በይሉኝታ አትጥፊ ቀኑ ቢገፋም ቤት ያፈራዉ ፍቅር መቼም ላንቺ አይጠፋም ለፍቅራችን ጥምረት ጐጆ ሰርቻለዉ እራሴን ልሰጥሽ ተዘጋጅቻለዉ ሞልቶ ባይርፈኝም ባልደላደልም ያለዉን የሰጠ ንፉግ አይባልም አምላክ በረዳኝ መጠን ስትመጪ እንዳላፍር ይዤ አጠብቅሻለዉ ብት ያፈራዉን ፍቅር ብቻ ነይ እንጂ ብቻ ነይ እንጂ ቤት ያፈራዉን ፍቅር አልነፍግ እንዳንቺ ብቻ ነይ እንጂ ብቻ ነይ እንጂ ቤት ያፈራዉን ፍቅር አልነፍግ እንዳንቺ የለም እንዳልልሽ ተዘጋጅቻለዉ (ብቻ) ጓዳዉን ደጁንም አሳምሬዋለዉ (ብቻ) ምንም ጊዜዉ ቢርቅ ምንም ቀን ቢገፋም (ብቻ) ለአንቺ ሚሆን ፍቅርምን ጊዜም አይጠቁርም ብቻ ነይ እንጂ ብቻ ነይ እንጂ ቤት ያፈራዉን ፍቅር አልነፍግ እንዳንቺ ብቻ ብቻ ብቻ ብቻ ነይ እንጂ ብቻ ነይ እንጂ ቤት ያፈራዉን ፍቅር አልነፍግ እንዳንቺ ብቻ ነይ እንጂ ብቻ ነይ እንጂ ቤት ያፈራዉን ፍቅር አልነፍግ እንዳንቺ ብቻ ነይ እንጂ ብቻ ነይ እንጂ ቤት ያፈራዉን ፍቅር አልነፍግ እንዳንቺ
Writer(s): Tsehaye Yohannes Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out