Lyrics

ሰበቤ ሁን ሲልህ ባንተ አርጎ ሰበብ ሰበቤ ሁን ሲልህ ባንተ አርጎ ሰበብ ደስታዬን ከመረው እንደ ድንጋይ ክብ አለም ሌላ መስሎኝ ብዙ ብዙ ስመኝ አለም ሌላ መስሎኝ ብዙ ብዙ ስመኝ መኖር ገና ጀመርኩ ከንፈርህ ሲስመኝ ይቀኝልኝ ነፍስህ ለነፍሴ ዝማሬ ይቀኝልኝ ነፍስህ ለነፍሴ ዝማሬ እድሜዬን ለካሁት በፍቅርህ ጅማሬ እድሜዬን ለካሁት በፍቅርህ ጅማሬ ይመስለኝ ነበር ድሮ ፍቅር የገራገር ይመስለኝ ነበር ድሮ ፍቅር የገራገር አፌን ፈታሁ ገና ስላንተ ስናገር ምን ቀረህ ልበልህ ፀጉሬንም ቆጥረሃል ምን ቀረህ ልበልህ ፀጉሬንም ቆጥረሃል ታሪኬን ገልብጠህ እንደ አዲስ ፈጥረሃል ውዴ የኔ ነህ ለነጠላ ነብሴ ተድላን የሞላህ ፍቅሬ ላንተ ነው እንደፀሃይ ጨረቃ ዘመኔን ላሰላው ሁሌ ይሁንልን ብራ ቀን ወረት እንደሰማይ ይራቀን ሁሌ ይሁንልን ብራ ቀን ወረት እንደሰማይ ይራቀን ያሳለፍኩት ዘመን ካላንተ ፍቅር ከዕድሜዬ ይሰረዝ ተቆርጦ ይቅር ፍቅር ከሞላበት የትም ሁን ይመቻል ፍቅር የጎደለው አለም ይሰለቻል የለመለመ ሰውነት ኧረ ያምራል ሰውነቴ ከንፈርህን ብጎርሰው አቅፌህ እንደናቴ አፍህ ከከንፈሬ ላፍታ ሳይነቀል ቀን እና ሌሊቱ አብሮ ይቀላቀላል አለም ያሳየሀኝ ስንቱ ይቆጠራል የፍቅር አባት ነህ ስሙ ባንተ ይጠራል ውዴ የኔነህ ለነጠላ ነብሴ ተድላን የሞላህ ፍቅሬ ላንተ ነው እንደፀሃይ ጨረቃ ዘመኔን ላሰላው ሁሌ ይሁንልን ብራ ቀን ወረት እንደሰማይ ይራቀን ሁሌ ይሁንልን ብራ ቀን ወረት እንደሰማይ ይራቀን ወረት እንደሰማይ እህ ኦ ኦ ኦ ኦ እህ እህ እህ እህ እህ አህ እህ እህ እህ
Writer(s): Elias Woldemariam, Mikaya Behailu Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out