Similar Songs
Credits
PERFORMING ARTISTS
Tsehaye Yohannes
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Tsehaye Yohannes
Songwriter
Lyrics
ሰዉ ያስባል ሳትይ ምነዉ በዚያዉ ጠፋሽ ምነዉ በዚያዉ ጠፋሽ
አንዴ ብቅ አልሽና ዉሃ ሆነ ሽታሽ ዉሃ ሆነ ሽታሽ
በይሉኝታ አትጥፊ ቀኑ ቢገፋም
ቤት ያፈራዉ ፍቅር መቼም ላንቺ አይጠፋም
ሰዉ ያስባል ሳትይ ምነዉ በዚያዉ ጠፋሽ ምነዉ በዚያዉ ጠፋሽ
አንዴ ብቅ አልሽና ዉሃ ሆነ ሽታሽ ዉሃ ሆነ ሽታሽ
በይሉኝታ አትጥፊ ቀኑ ቢገፋም
ቤት ያፈራዉ ፍቅር መቼም ላንቺ አይጠፋም
ቀድሞም የሰዉ ነገር አንቺን ይከብድሻል
ዛሬም በይሉኝታ ከኔ ጋ ርቀሻል
ብዙም ባይጋነን ብዙ ባያኮራ
አንቺን ለመቀበል ከጐጆዬ ጋራ
ንፁህ ልቤን አስፍቼ ለመጪዉ ፍቅር ዘመን
ዝግጁ ነኝ ምን ጊዜም አምኜሽ ለመታመን
ብቻ ነይ እንጂ ብቻ ነይ እንጂ
ቤት ያፈራዉን ፍቅር አልነፍግ እንዳንቺ
ብቻ ነይ እንጂ ብቻ ነይ እንጂ
ቤት ያፈራዉን ፍቅር አልነፍግ እንዳንቺ
የለም እንዳልልሽ ተዘጋጅቻለዉ (ብቻ)
ጓዳዉን ደጁንም አሳምሬዋለዉ (ብቻ)
ምንም ጊዜዉ ቢርቅ ምንም ቀን ቢገፋም (ብቻ)
ለአንቺ ሚሆን ፍቅርምን ጊዜም አይጠቁርም
ብቻ ነይ እንጂ ብቻ ነይ እንጂ
ቤት ያፈራዉን ፍቅር አልነፍግ እንዳንቺ
ሰዉ ያስባል ሳትይ ምነዉ በዚያዉ ጠፋሽ ምነዉ በዚያዉ ጠፋሽ
አንዴ ብቅ አልሽና ዉሃ ሆነ ሽታሽ ዉሃ ሆነ ሽታሽ
በይሉኝታ አትጥፊ ቀኑ ቢገፋም
ቤት ያፈራዉ ፍቅር መቼም ላንቺ አይጠፋም
ለፍቅራችን ጥምረት ጐጆ ሰርቻለዉ
እራሴን ልሰጥሽ ተዘጋጅቻለዉ
ሞልቶ ባይርፈኝም ባልደላደልም
ያለዉን የሰጠ ንፉግ አይባልም
አምላክ በረዳኝ መጠን ስትመጪ እንዳላፍር
ይዤ አጠብቅሻለዉ ብት ያፈራዉን ፍቅር
ብቻ ነይ እንጂ ብቻ ነይ እንጂ
ቤት ያፈራዉን ፍቅር አልነፍግ እንዳንቺ
ብቻ ነይ እንጂ ብቻ ነይ እንጂ
ቤት ያፈራዉን ፍቅር አልነፍግ እንዳንቺ
የለም እንዳልልሽ ተዘጋጅቻለዉ (ብቻ)
ጓዳዉን ደጁንም አሳምሬዋለዉ (ብቻ)
ምንም ጊዜዉ ቢርቅ ምንም ቀን ቢገፋም (ብቻ)
ለአንቺ ሚሆን ፍቅርምን ጊዜም አይጠቁርም
ብቻ ነይ እንጂ ብቻ ነይ እንጂ
ቤት ያፈራዉን ፍቅር አልነፍግ እንዳንቺ
ብቻ ብቻ ብቻ
ብቻ ነይ እንጂ ብቻ ነይ እንጂ
ቤት ያፈራዉን ፍቅር አልነፍግ እንዳንቺ
ብቻ ነይ እንጂ ብቻ ነይ እንጂ
ቤት ያፈራዉን ፍቅር አልነፍግ እንዳንቺ
ብቻ ነይ እንጂ ብቻ ነይ እንጂ
ቤት ያፈራዉን ፍቅር አልነፍግ እንዳንቺ
Writer(s): Tsehaye Yohannes
Lyrics powered by www.musixmatch.com