Lyrics

አሀሀሀሀ... ስለ ፍቅር ሲባል ስለ ፀብ ካወራን ተሳስተናል አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል አጥተናል እውነት ነው ተቸግረን ብዙ አይተናል የመጣነው መንገድ ያሳዝናል እግር ይዞ እንዴት አይሄድም ሰው ወደፊት አይራመድም አፈር ይዞ ውስጡ አረንጓዴ ለምን ይሆን የራበው ሆዴ ብራናው ይነበብ ተዘርግቶ በአትሮነሱ ላይ የነ ፋሲለደስ የነ ተዋናይ የት ጋር እንደሆነ ይታይ የኛ ጥበብ መሰረቱ የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ ሳይራመድ በታሪክ ምንጣፍ ሰው አይደርስም ከዛሬ ደጃፍ አፈር ይዞ ውስጡ አረንጓዴ ለምን ይሆን የራበው ሆዴ ከአድማስ እየራቀ ምነው ይሄ መንገድ ያባክነኛል በየት በኩል ብሄድ ወደ እረፍት ሃገሬ ቶሎ ያደርሰኛል ቀስተ ዳመና ነው የለበስኩት ጥበብ የያዝኩት አርማ አልጠላም ወድጄ የነፍሴ ላይ ፋኖስ እንዳያይ ጨለማ አንተ አብርሃም የኦሪት ስብሐት የነ እስማኤል የይስሀቅ አባት ልክ እንደ አክሱም ራስ ቀርፀሃት ራሴን በፍቅር ጧፍ ለኩሳት ነፍሴን በል አትዛል ቀና ሁን ልቤ የሕልሜን ከነዓን እንዳይ ቀርቤ ሰው ለመውደድ ካልኩኝ ደከመኝ ያኔ ገና ውስጤን አመመኝ አመመኝ አመመኝ እኔን አመመኝ አመመኝ አመመኝ እኔን አመመኝ ያኔ ገና ውስጤን አመመኝ ያኔ ገና ውስጤን አመመኝ እኔን አመመኝ እኔን አመመኝ እኔን አመመኝ እኔን አ አሀሀሀሀ... ስለ ፍቅር ሲባል ስለ ፀብ ካወራን ተሳስተናል አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል አጥተናል እውነት ነው ተቸግረን ብዙ አይተናል የመጣነው መንገድ ያሳዝናል እግር ይዞ እንዴት አይሄድም ሰው ወደፊት አይራመድም አፈር ይዞ ውስጡ አረንጓዴ ለምን ይሆን የራበው ሆዴ የኦርዮን ኮኮብ የሩቅ ሰማይ መንገድ የሌት በራሪ የልቤን አርጋኖን በደመናው መስኮት ዘልቀሽ ንገሪ ቀስተ ዳመና ነው የለበስኩት ጥበብ የያዝኩት አርማ አልጠላም ወድጄ የነፍሴ ላይ ፋኖስ እንዳያይ ጨለማ አንተ አብርሃም የኦሪት ስብሐት የነ እስማኤል የይስሀቅ አባት ልክ እንደ አክሱም ራስ ቀርፀሃት ራሴን በፍቅር ጧፍ ለኩሳት ነፍሴን በል አትዛል ቀና ሁን ልቤ የሕልሜን ከነዓን እንዳይ ቀርቤ ሰው ለመውደድ ካልኩኝ ደከመኝ ያኔ ገና ውስጤን አመመኝ አመመኝ አመመኝ እኔን አመመኝ አመመኝ አመመኝ እኔን አመመኝ ያኔ ገና ውስጤን አመመኝ ያኔ ገና ውስጤን አመመኝ እኔን አመመኝ እኔን አመመኝ እኔን አመመኝ እኔን አ አሀሀሀሀ...
Writer(s): Teddy Afro Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out