Lyrics

እንኳን አገኘሁሽ እንኳን ደና ቆየሽ እኔስ መስሎኝ ነበር ፈልጌ ማጣሽ እቴ የልጅነቴ የልጅነቴ እንዴት ነሽ እቴ የልጅነቴ የልጅነቴ እንዴት ነሽ አይወስድሽም እያሉ ሲዘፍኑብሽ በይፋ በነገር ባሽሙራቸው እቴ አንገትሽ ሲደፋ ያ የጠበኩት ፍቅሬ ይኸው መጣ በያቸው ይዟት ይዟት በረረ እስቲ ሲሉ እንስማቸው የሄደ ሰው አይቀር እርቆ ይመለሳል ጊዜ ጠብቆ ከሩቅ ሀገር ስመጣ ቤትሽ አልተነካም ቃል እና እምነትሽ እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ ከዚህ በላይ ምን አለ ደስታ እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ ከዚህ በላይ ምን አለ ደስታ እንኳን አገኘሁሽ እንኳን ደና ቆየሽ እኔስ መስሎኝ ነበር ፈልጌ ማጣሽ እቴ የልጅነቴ የልጅነቴ እንዴት ነሽ እቴ የልጅነቴ የልጅነቴ እንዴት ነሽ እርሳት ይሉኝ ነበረ የሩቅ ሰው በማፍቀሬ ከንቱ ነበር ለነሱ ቃልኪዳኔን ማክበሬ ዛሬ ተገናኝተናል የምስራች ይነገር አምሯል ሸገኑ ብሎ አዎ እስቲ ይሸኘን ሀገር የሄደ ሰው አይቀር እርቆ ይመለሳል ጊዜ ጠብቆ ከሩቅ ሀገር ስመጣ ቤትሽ አልተነካም ቃል እና እምነትሽ እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ ከዚህ በላይ ምን አለ ደስታ እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ ከዚህ በላይ ምን አለ ደስታ ከቤቴ በላይ ፍቅር ሰፍሮ ፍቅር ሰፍሮ ትዝታው መጣ ይኸው በሮ ይኸው በሮ እኔን ሲያበረኝ ሲያከንፈኝ ሲያከንፈኝ ከወጣሁበት አመጣኝ አመጣኝ ከመጣውማ ወደ ቤቴ ወደ ቤቴ አንቺን ካገኘው እመቤቴን እመቤቴን የኔ እመቤት አትለይኝ እስከ ዘላለም ያንቺው ነኝ ያንቺው ነኝ የሄደ ሰው አይቀር እርቆ ይመለሳል ጊዜ ጠብቆ ከሩቅ ሀገር ስመጣ ቤትሽ አልተነካም ቃል እና እምነትሽ እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ ከዚህ በላይ ምን አለ ደስታ እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ ከዚህ በላይ ምን አለ ደስታ
Writer(s): Abdu Kahssay Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out