Lyrics

ከኔ ርቀሽ ለመሄድ ማሰብሽን እንደ ሩቅ ሰው በድንገት ሰማሁና እንዳልጠይቅሽ ደፍሬ አንቺን ደሞ ምየልሻለው ወሬ እንደማልሰማ ታድያ የቤቴን ገመና ማያቅ ሰው ሲነግረኝ ሂድ ብዬ እንዴት ልመልሰው ቀንቶ ነው አልል በቅርበት አያውቀኝም ኧረ የሰማሁት ውሸት አይመስለኝም እንድንነጋገር እስኪ አንዴ አረፍ በይ ወደቤት ወደቤት የሚያስሮጠኝ ጉዳይ ባንቺ አይደለም ወይ እኔን ጥሎ መሄድ ታድያ አይከብድሽም ወይ በፍቅር በመውደድ ያሳለፍነው ጊዜ እውነት አይደለም ወይ (ልቤ ደሞ) ተሰቃይተህ በሷ (ልቤ ደሞ) ጭንቅ አትደርብብኝ (ልቤ ደሞ) ቆይ ከሷ ይምጣ ልቤ ደሞ (ልቤ ደሞ) እስኪ አትቸኩልብኝ ደርሶ አትዘንብኝ (ልቤ ደሞ) የመንደሩን ወሬ (ልቤ ደሞ) አሳልፌ ለሷ (ልቤ ደሞ) ብነግራት ታዝናለች ደሞ (ልቤ ደሞ) ሰው እንደማልሰማ የማልኩላትን አስታውሳ ከኔ ርቀሽ ለመሄድ ማሰብሽን እንደ ሩቅ ሰው በድንገት ሰማሁና እንዳልጠይቅሽ ደፍሬ አንቺን ደሞ ምየልሻለው ወሬ እንደማልሰማ ታድያ የቤቴን ገመና ማያቅ ሰው ሲነግረኝ ሂድ ብየ እንዴት ልመልሰው ቀንቶ ነው አልል በቅርበት አያውቀኝም ኧረ የሰማሁት ውሸት አይመስለኝም ልምዱ አለሽ አይደል ወይ ሲከፋሽ መናገር እስኪ እንዴት በድንገት ማን አስተማረብኝ የሚያስደብቅ ነገር ከኔ እንደምትርቂ ሲወራ ባገሩ ኧረ እንዴት ኧረ እንዴት እሱ አልሰማም ብሎ ያማኛል መንደሩ (ልቤ ደሞ) ተሰቃይተህ በሷ (ልቤ ደሞ) ጭንቅ አትደርብብኝ (ልቤ ደሞ) ቆይ ከሷ ይምጣ ልቤ ደሞ (ልቤ ደሞ) እስኪ አትቸኩልብኝ ደርሶ አትዘንብኝ (ልቤ ደሞ) የመንደሩን ወሬ (ልቤ ደሞ) አሳልፌ ለሷ (ልቤ ደሞ) ብነግራት ታዝናለች ደሞ (ልቤ ደሞ) ሰው እንደማልሰማ የማልኩላትን አስታውሳ ሰው ተላምዶ እንዴት ይጎዳል መሰለሽ መለየት ወዶ ክፉ ቅጣት እንዴት ይጎዳል መሰለሽ አግኝቶ ማጣት እያለው በቁሜ ከራቅሺኝማ ምኑን ከምኔ ስትሄጅ ሊስማማ ልትሄጅ ነው እንዴ ሰውነቴ አንቺን ለምዶ ፍቅር አለሽ ከቤት ይቅር አትሂጂ ማዶ እያለው በቁሜ ከራቅሺኝማ ምኑን ከምኔ ስትሄጅ ሊስማማ ልትሄጅ ነው እንዴ ጎኔ አንቺን ለምዶ ፍቅር አለሽ ከቤት ይቅር አትሂጂ ማዶ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out