Lyrics

ተጭኖብኝ ፡ የማልችለውን የሞት ፡ ፍርሀት ፡ አርጎኝ ፡ ምስኪን መች ፡ አገዝኝ ፡ የእኔነት ፡ ካባዬ አልቆ ፡ ነበር ፡ የመኖር ፡ ተስፋዬ ግን ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ወንጌል ፡ ሰማሁኝ ይታደጋል ፡ ያድናል ፡ ሲሉኝ በቅንነት ፡ እጄን ፡ አነሳሁኝ የዛች ፡ ለት ፡ ጌታን ፡ አገኘሁኝ አዲስ ፡ ነገር ፡ የዛች ፡ ለት ፡ ሆነ (፪x) በመንፈሴ ፡ ሰላም ፡ ሰፈነ (፪x) አፈሰሰው ፡ በልቤ ፡ ደስታ (፪x) መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ የሰላም ፡ ጌታ (፪x) በአገር ፡ በሰፈሩ ፡ እታማ ፡ ጀመረ የእናት ፡ እና ፡ የአባቱን ፡ ሃይማኖት ፡ ቀየረ ይህን ፡ ያንን ፡ ብለው ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ተነሱ እኔ ፡ የቀመስኩትን ፡ ምነው ፡ በቀመሱ ኢየሱስ ፡ ብቸኛ ፡ አማራጭ ፡ የሌለው ወደ ፡ ሰማይ ፡ መግብያ ፡ ብቸኛ ፡ መንገድ ፡ ነው ያዳነኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው የሞተልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው በመስቀል ፡ ላይ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው የተወጋልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ዋጋ ፡ ከፍሎ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው በደም ፡ ገዛኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ከጻድቃን ፡ ጋር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው የቀላቀለኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው መዘበቻ ፡ አርጓት ፡ ነፍሴን ፡ ሰይጣን ፡ ክፉ ፡ አይራራ ፡ አያዝን ከሱ ፡ ለማምለጥ ፡ ብዙ ፡ ጣርኩኝ ፡ ግን ፡ አልቻልኩኝ በዚህ ፡ ሁኔታ ፡ ወንጌል ፡ ሰማሁኝ ፡ እየሱስን ፡ ተገናኘሁኝ ሰው ፡ መሆኔን ፡ የወደድኩት ፡ ያየሁት ፡ ለት የልጅነትን ፡ ሥልጣንን ፡ ሰጠኝ ፡ ሥልጣን ፡ ሰጠኝ ያሳደደኝን ፡ አሳደድኩኝ ፡ አሳደድኩኝ የበቀል ፡ ቅባት ፡ እራሴን ፡ ቀባኝ ፡ እራሴን ፡ ቀባኝ ያስጨነቀኝን ፡ አስጨነኩኝ ፡ አስጨነኩኝ እናንተ ፡ ደካሞች ፡ ሸክማቹህ ፡ ከባድ ወደ ፡ እኔ ፡ ኑ ፡ ያለ ፡ ይሄ ፡ ሰውን ፡ ወዳጅ ያሳረፈኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ሰው ፡ ያደረገኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ያከበረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ያዘመረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ዋጋ ፡ ከፍሎ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው በደም ፡ ገዛኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ከጻድቃን ፡ ጋር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው የቀላቀለኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
Writer(s): Samuel Alemu, Bereket Tesfaye Unknown Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out