Lyrics

ለካ ይታለፋል ማይታለፈው ከልኩ አያልፍም የሰው ፈተናው ምጠፋ መስሎኝ ፈራች እንጂ ነፍሴ ለካ ያስጨነከኝ ለጥቅሜ ለራሴ በእሳት እያለፍኩ ስፈተን ወርቅ አደረገው ህይወቴን በእሳት እያለፍኩ ስፈተን ወርቅ አደረገው ህይወቴን ጌታ ሆይ አሁን ተማርኩ ተስተካከልኩ አመፃን ጥዬ ፅድቅንም ያዝኩ ያ ልፍስፍሱ ጠነከረ እንጂ ልቤ አላጠፋኝም የጋለው ከአጠገቤ ተስማምቶ የኖረ ከአፈር እና ከጭቃ እሳት ሲያገኘው ሆነ የክብር ዕቃ ጠንክሬ በርትቼ እንድመላለስ ልቤን አጀገነው ቅዱሱ መንፈስ ቀዝቃዛ ህይወቴ በፈተናው ሞቀ እሳቱ ሲነካው ነጠረ ደመቀ ዘመኔ እንዲደምቅ እንዲያበራ መቼ መሰለኝ የምሰራ ልክ እንደ ድንጋይ ተራ የነበረ እሳት ሲያገኘው ሆነ የከበረ (ለመልካም ሆነልኝ ሆነልኝ) (ለመልካም ሆነልኝ ሆነልኝ) (ለበጎ ሆነልኝ ሆነልኝ) (ለበጎ ሆነልኝ ሆነልኝ) ሆነልኝ ሆነልኝ (ለመልካም) ሆነልኝ ያስጨነከኝ (ለመልካም) ሆነልኝ ሆነልኝ (ለበጎ) ሆነልኝ ያስጨነከኝ (ለበጎ) በመከራ ውስጥ መታዘዝን ተማረ በስጋው ወራት አንተን አከበረ እኛ ዳንን እንጂ በእርሱ መከራ ህይወታችን ጣፍጧል በጠጣው መራራ እሱ ኃያል ሳለ ምስኪን መሰለ ከአመፀኞች ጋር ተሰቀለ በጌታ መከራ ስንቶች ዳኑ አቀረባቸው ወደ ዙፋኑ ጌታ ሆይ አሁን ተማርኩ ተስተካከልኩ አመፃን ጥዬ ፅድቅንም ያዝኩ ያ ልፍስፍሱ ጠነከረ እንጂ ልቤ አላጠፋኝም የጋለው ከአጠገቤ ተስማምቶ የኖረ ከአፈር እና ከጭቃ እሳት ሲያገኘው ሆነ የክብር ዕቃ ጠንክሬ በርትቼ እንድመላለስ ልቤን አጀገነው የጌታ መንፈስ ቀዝቃዛ ህይወቴ በፈተናው ሞቀ እሳቱ ሲነካው ነጠረ ደመቀ ዘመኔ እንዲደምቅ እንዲያበራ መቼ መሰለኝ የምሰራ ልክ እንደ ድንጋይ ተራ የነበረ እሳት ሲያገኘው ሆነ የከበረ (ለመልካም ሆነልኝ ሆነልኝ) (ለመልካም ሆነልኝ ሆነልኝ) (ለበጎ ሆነልኝ ሆነልኝ) (ለበጎ ሆነልኝ ሆነልኝ) ሆነልኝ ሆነልኝ (ለመልካም) ሆነልኝ ያስጨነከኝ (ለመልካም) ሆነልኝ ሆነልኝ (ለበጎ) ሆነልኝ ያስጨነከኝ (ለበጎ)
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out