Lyrics

ይመቸኛል ካንቺ ጋር ጨዋታ አይጥመኝም እጠላለው ዝምታ በይ አናግሪኝ አንደበትሽ ይልመድ እንድንዋደድ አንደኛዬ የልቤ መድረሻ እንግዳዬ የፍቅሬ መነሻ አልተውሽም እኔ እነግርሻለው እወድሻለው ሚስጥሬን ነግሬ ካልወጣልኝ ማፍቀር ለብቻዬ ምን ሊረባኝ ልናገረው፣እንጫወት ካፈቀርኩሽ የምን ስስት እስኪ ባንደበቴ ልናገረው ሆዴ እንዲተነፍስ እንዲቀለው ካሉኝ አይቀር፣አበደላት የሷን ፍቅር፣ላውጅላት የኔ የኔ የኔ ነሻ ከቃል በላይ ጭንቄን መርሻ ቀዳማዊት እመቤቴ የግልሽ ነው ኑሪ ቤቴ የኔ የኔ የኔ ነሻ ከቃል በላይ ጭንቄን መርሻ ቀዳማዊት እመቤቴ የግልሽ ነው ግቢ ቤቴ ይመቸኛል ካንቺ ጋር ጨዋታ አይጥመኝም እጠላለው ዝምታ በይ አናግሪኝ አንደበትሽ ይልመድ እንድንዋደድ አንደኛዬ የልቤ መድረሻ እንግዳዬ የፍቅሬ መነሻ አልተውሽም እኔ እነግርሻለው እወድሻለው ሙሉ አይደለምና ሰው በራሱ የሚወደው አለው እንደ ነፍሱ ካፍሽ ፍሬ ልብላ ከከንፈርሽ አይንሽ ስር ቁጭ ብዬ ሁሌ እንዳይሽ በዝች መንገድ ዓለም ልታርፊባት በልብሽ እፎይን አትንፈጊያት አንችን ደስ ብሎሽ ተሳክቶልኝ እኔም በተራዬ ዝም ባልኩኝ የኔ የኔ የኔ ነሻ ከቃል በላይ ጭንቄን መርሻ ቀዳማዊት እመቤቴ የግልሽ ነው ግቢ ቤቴ የኔ የኔ የኔ ነሻ ከቃል በላይ ጭንቄን መርሻ ቀዳማዊት እመቤቴ የግልሽ ነው ግቢ ቤቴ የኔ የኔ የኔ ነሻ ከቃል በላይ ጭንቄን መርሻ ቀዳማዊት እመቤቴ የግልሽ ነው ግቢ ቤቴ ኦሆሆ ላ ላ ላ ላ ኦሆሆ ኦሆሆ ላ ላ ላ ላ ኦሆሆ ላ ላ ላ ላ
Writer(s): Elias Woldemariam, Eiyubel B Birhanu, Yilma G/ab Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out