Lyrics

ከሲዖል መውጣቴ ይበቃኝ ነበረ በዚያ አላበቃም ፍቅሩ ጨመረ ቀረበኝ አልሆንኩም ብቸኛ አምላኬ ልክ እንደ ጓደኛ ሳይዘው ሳይገድበው ትልቅነቱ አብሮኝ ነው ኢየሱስ ትሁቱ የቅርቤ ልበልህ የቅርቤ የቅርቤ ልበልህ የቅርቤ ከእስትንፋሴ ይልቅ የቅርቤ የቅርቤ ልበልህ የቅርቤ ከእስትንፋሴ ይልቅ ይልቅ የቅርቤ ነህ ፊትህን ተርቤ መቼ መቼ አጣሁህ የሆድ የውስጤን ታውቀው የለም ወይ ሳልተነፍስ ውዴ ኢየሱስ ሰው ሚያውቀው ጉብዝናዬን መቼ አየ ገመናዬን ሸፍነኸው ጉድለቴን ሚታየው ግን ሙላቴ የቅርቤ ልበልህ የቅርቤ የቅርቤ ልበልህ የቅርቤ ከእስትንፋሴ ይልቅ የቅርቤ የቅርቤ ልበልህ የቅርቤ ዞር ብዬ ወደ ኋላ መንገዴን ሳይ የአንተ እንጂ የእኔ ኮቴ አይታይ አባጣ ጎርባጣውን እኔ መውጣቴ ይዘኸኝ ልክ እንደ እናቴ ምንም ባሳዝንህ በድካሜ ታግሰህ አቆምከኝ መድህኔ ሰው ሚያውቀው ጉብዝናዬን መቼ አየ ገመናዬን ሸፍነኸው ጉድለቴን ሚታየው ግን ሙላቴ በሰዎች መሐል ወይም ለብቻዬ ድምፁን ያሰማኛል አብሮኝ ነው ጌታዬ በዚህ ሂድ በዚያ ሂድ እያለኝ ጠላት የማሰውን አለፍኩኝ አምላኬ የመከረኝን ሰምቼው አለፍኩኝ ስንቱን የቅርቤ ልበልህ የቅርቤ የቅርቤ ልበልህ የቅርቤ ከእስትንፋሴ ይልቅ የቅርቤ የቅርቤ ልበልህ የቅርቤ ሰው ሚያውቀው ጉብዝናዬን መቼ አየ ገመናዬን ሸፍነኸው ጉድለቴን ሚታየው ግን ሙላቴ የቅርቤ ልበልህ የቅርቤ የቅርቤ ልበልህ የቅርቤ ከእስትንፋሴ ይልቅ የቅርቤ የቅርቤ ልበልህ የቅርቤ
Writer(s): Samuel Alemu, Bereket Tesfaye Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out