Lyrics

ተበድዬስ ይቅርታ አልልም የቀረው ይቅር እንጂ ተበድዬስ ማሪኝ አልልም የቀረው ይቅር እንጂ እንኳን ልልክ አማላጅ እግሬ አይረግጥም ያንቺን ደጅ ተበድዬስ ይቅርታ አልልም የቀረው ይቅር እንጂ ተበድዬስ ማሪኝ አልልም የቀረው ይቅር እንጂ እንኳን ልልክ አማላጅ እግሬ አይረግጥም ያንቺን ደጅ እንኳን ልልክ አማላጅ እግሬ አይረግጥም ያንቺን ደጅ አፍቅሬህ ኖራለው ስትይኝ ከርመሻል ታምኜ ዘልቃለው ስትይኝ ከርመሻል ያኔ ባንደበትሽ ፅኑ ሰው መስለሻል ቃልሽ የታጠፈው ዛሬ ምን ነክቶሻል ከአካሌ መለየት መራቁን ስትመርጪ ሸርተት እያልሽብኝ ከእቅፌ ስትወጪ ልቤን እየከፋው ላሰናብትሽ እንጂ ትከትዬ አልመጣም ጥለሺኝ ስትሄጂ በደል ያሻከረው ሆዴን ላታባቢ የጨከነ አንጀቴን ችለሽ ላታባቢ የማይሽር ጥላቻን በኔ ልብ አፍርተሽ በእምባ መማፀኑን አታስቢ ደፍረሽ የት ነበርሽ የት ነበርሽ የት ነበርሽ የት ነበርሽ ተበድዬስ ይቅርታ አልልም የቀረው ይቅር እንጂ ተበድዬስ ማሪኝ አልልም የቀረው ይቅር እንጂ እንኳን ልልክ አማላጅ እግሬ አይረግጥም ያንቺን ደጅ ተበድዬስ ይቅርታ አልልም የቀረው ይቅር እንጂ ተበድዬስ ማሪኝ አልልም የቀረው ይቅር እንጂ እንኳን ልልክ አማላጅ እግሬ አይረግጥም ያንቺን ደጅ እንኳን ልልክ አማላጅ እግሬ አይረግጥም ያንቺን ደጅ ስታጠፊ ኖረሽ ስታገስሽ ኖሬ ስንቱን ጊዜ አለፍኩት ቀን በቀን መክሬ ያንቺ ነገር ባይሆን እየፈጩ ጥሬ ደክሜልሽ ነበር እኔስ እስከዛሬ በእድሜ ሳይገደብ ከልጅ እስከ አዋቂ የበደለ ሰው ነው ይቅርታ ጠያቂ መቻሌ ሳያንሰኝ የጥፋትሽ ህመም እንደው ምን አርጌሽ ይቅር በይኝ ልበል ዛሬ ህሊናሽ ወቅሶሽ ምንም ብትቆጪ በደልሽ አጥሮሻል መቼም ከኔ አትመጪ የፀፀት መንገዱን ጎዳናው ከታየሽ ምህረት ባልነፍግሽም አንቺ ግን ዘገየሽ የት ነበርሽ የት ነበርሽ የት ነበርሽ የት ነበርሽ የት ነበርሽ የት ነበርሽ የት ነበርሽ የት ነበርሽ የት ነበርሽ የት ነበርሽ የት ነበርሽ የት ነበርሽ
Writer(s): Tsehaye Yohannes Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out