Lyrics

ባትኖርም ካጠገቤ ከጎኔ ብትለየኝም እኔስ አይሃለሁ አንተ ባታየኝም ሳየው ሳየው ባድር ብዉል አይወጣልኝም ፍቅር ያንተስ ፍቅር ፍቅር ያንተስ ፍቅር ካጠገብህ ሁኜ ባላጫዉትህም ገላህን አቅፌ ምንም ባልስምህም በመንፈስ ካንተዉ ነኝ መቼም አልለይም በሃሳብ መነጸር ሁሌ ነዉ የማይህ ዉቅያኖስ ባህሩ አድማስ ቢጋርደኝ ወዳንተ መምጣቴን ማንም አያግደኝ መምጫ መንገድ ሁሉ ቢዘጋ ቢታገድ ፍቅር ያደርሰኛል ባሳብ አየር መንገድ የኔ ፍቅር ፍቅር አገናኝተህ ከምትለየኝ የኔ ፍቅር ፍቅር ምነዉ በፊት ባታሳየኝ የኔ ፍቅር ፍቅር ወይ ዉሰደኝ ወይ አምጣልኝ የኔ ፍቅር ፍቅር ያለዚያማ ጉዴ ነዉ እንጃልኝ የኔ ፍቅር ፍቅር አገናኝተህ ከምትለየኝ የኔ ፍቅር ፍቅር ምነዉ በፊት ባታሳየኝ የኔ ፍቅር ፍቅር ወይ ዉሰደኝ ወይ አምጣልኝ የኔ ፍቅር ፍቅር ያለዚያማ ጉዴ ነዉ እንጃልኝ የኔ ፍቅር የኔ ፍቅር የኔ ፍቅር የኔ ፍቅር ባትኖርም ካጠገቤ ከጎኔ ብትለየኝም እኔስ አይሃለሁ አንተ ባታየኝም ሳየው ሳየው ባድር ብዉል አይወጣልኝም ፍቅር ያንተስ ፍቅር ፍቅር ያንተስ ፍቅር ቀኑን በትካዜ ብቻየን ሳወራ ደግሞ ሊተካልኝ ሌሊቱም በተራ ገና ገደም እንዳልኩ ካልጋዉ ስንገናኝ የሃሳብ ሰመመን ጉዞ ነዉ የሚቀናኝ ድንገት ከተፍ ስል ካለህበት ቦታ እየተላቀስን በናፍቆት በደስታ ታዲያ ምን ያደርጋለ ነበር ቢሆን በዉኔ ለካስ በህልሜ ነዉ የማገኝህ እኔ የኔ ፍቅር ፍቅር እዉን አርገዉ ፍታዉ ህልሜን የኔ ፍቅር ፍቅር እንድወጣዉ ርሃብ ጥሜን የኔ ፍቅር ፍቅር ወይ ዉሰደኝ ወይ አምጣልኝ የኔ ፍቅር ፍቅር ያለዚያማ ጉዴ ነዉ እንጃልኝ የኔ ፍቅር ፍቅር እዉን አርገዉ ፍታዉ ህልሜን የኔ ፍቅር ፍቅር እንድወጣዉ ርሃብ ጥሜን የኔ ፍቅር ፍቅር ወይ ዉሰደኝ ወይ አምጣልኝ የኔ ፍቅር ፍቅር ያለዚያማ ጉዴ ነዉ እንጃልኝ የኔ ፍቅር ፍቅር እዉን አርገዉ ፍታዉ ህልሜን የኔ ፍቅር ፍቅር እንድወጣዉ ርሃብ ጥሜን የኔ ፍቅር ፍቅር ወይ ዉሰደኝ ወይ አምጣልኝ የኔ ፍቅር ፍቅር ያለዚያማ ጉዴ ነዉ እንጃልኝ የኔ ፍቅር
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out