Lyrics

የሉም ሲባል ይኖራሉ ሁሁሁ ፣ ጠፉ ሲባል ይበዛሉ ሁሁሁ ሲዋለዱ ብዙ መኝታ ሃሃሃ ፣ ሩጫቸውን ማን ሊገታ ሃሃሃ አይታክቱም ፣ ይሄዳሉ ፣ አይደክሙም ይበረታሉ እንደ ንስር ፣ ይበራሉ ፣ እጥፍ-ድርብ ያፈራሉ እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራው ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀው እርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለው ባለም ምድረበዳ በድል የመራው የታደለ ምስጉን ነው በሰው ብልሃት የተሰራ ሃሃሃ ፣ በስጋ ደም የሚመራ ሃሃሃ ሀሳብ-ወለድ ፍልስፍና ሃሃሃ ፣ እምነታቸው መች ሆነና ሃሃሃ ይናገሩ ፣ ያዳናቸው ፣ እንደ ሰማይ ክዋክብት ናቸው ዲያቢሎስም ፣ ያውቃቸዋል ፣ ጊዜ ስጡኝ ይላቸዋል እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራው ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀው እርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለው ባለም ምድረበዳ በድል የመራው የታደለ ምስጉን ነው እሳት አለ በውስጣቸ-ኸኸ-ኸው ፣ ማንም አይችል ሊያጠፋቸ-ኸኸ-ኸው አይቻሉም ሲነኳቸ-ኸኸ-ኸው ፣ ተዋጊ ነው አምላካቸ-ኸኸ-ኸው ሰባኪዎች ፣ በመገለጥ ፣ ለዲያቢሎስ እሳት ረመጥ ዘማሪዎች ፣ በበገና ፣ ይቀባሉ ገና ገና እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራው ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀው እርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለው ባለም ምድረበዳ በድል የመራው የታደለ ምስጉን ነው ሠይፍ አይዙም በእጃቸ-ኸኸ-ኸው ፣ የመንፈስ ነው መሳሪያቼ-ሄሄ-ሄው እዩት እስቲ ይህን ምርኮ ሆሆሆ ፣ መንገደኛ አይደለም እኮ ሆሆሆ የክርስቶስ ፣ ስም ያዳነው ፣ የካህናት መንግስት ነው ያለም ብርሃን ፣ የምድር ጨው ፣ እንደ ከዋክብት የተረጨው እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራው ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀው እርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለው ባለም ምድረበዳ በድል የመራው የታደለ ምስጉን ነው ሟርት አይስራም በእስራኤል ላ-ሃሃ-ሃይ ፣ አስማት የለም በያዕቆብ ላይ ሄሄሄ አይቆጠርም ብዛቱ ሁሁሁ ፣ ድንበር የለው ለግዛቱ ሆሆሆ እግዚአብሔር ፣ እፍፍ ያለበት ፣ የፈጠረው ለበረከት መዳኒት ነው ፣ መፈወሻ ፣ ወስን የለው መጨረሻ እግዚአብሔር በልጁ ሞት የጠራው ከነገድ ከቋንቋ ከህዝብ የዋጀው እርስቴ ነህ ህዝቤ ገንዘቤ ያለው ባለም ምድረበዳ በድል የመራው የታደለ ምስጉን ነው
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out