Lyrics

ያሬድ ነጉ ከጉራጌ ባወጣኝ እግሬ ከመርካቶ ጎጃም በርሬ የትም ብሄድ ሁሉም ሀገሬ ለፍቶ አዳሪ ጠንካራ ዘሬ ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም አለመድሽኝና አስከ ጥግ ድረስ ቀረው ሳልመለስ ያውቅበታል ጎጃም እንዳባይ ማስመጡን ፍቅር ማጣፈጡን ብደክም ብለፋ መች ይሰለቸኛል መለኛው ጎጃሜ ማኛውን ሰቶኛል መቼም አይታማ ጉራጌ ለስራ ጎጃምም አላጣም ፍቅርና እንጀራ እንጀራም እንጀራ ፍቅርም ሀገር የለው አቤት ሲያገጣጥም እህል ውሀ እንዲህ ነው የሰርጋችን ድግስ ጎጃም ላይ ከሆነ ተመታ መሬቱ አቧራው ቦነነ አንተዬ እስቲ ባህልህን ልየው ጭፈራህን ላሳይሽ አንቺዬ ጎጃሜነትሺ ያምራል ትከሻሺ ከጉራጌ ባወጣኝ እግሬ ከመርካቶ ጎጃም በርሬ የትም ብሄድ ሁሉም ሀገሬ ለፍቶ አዳሪ ጠንካራ ዘሬ ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም ለፍቶ አዳሪው ልቤ ማርዬን አግኝቶ ቀረ ጎጃም ገብቶ በዘፈን በዝና የሰማሁት ሁሉ ለጎጃም ያንሳሉ ብደክም ብለፋ መች ይሰለቸኛል መለኛው ጎጃሜ ማኛውን ሰቶኛል መቼም አይታማ ጉራጌ ለስራ ጎጃምም አላጣም ፍቅርና እንጀራ እንጀራም እንጀራ ፍቅርም ሀገር የለው አቤት ሲያገጣጥም እህል ውሀ እንዲህ ነው የሰርጋችን ድግስ ጎጃም ላይ ከሆነ ተመታ መሬቱ አቧራው ቦነነ ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም ከጉራጌ ጎጃም ወይ ፍቅር ሲጣጣም
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out