Lyrics

ጥንትም ላይሆንልሽ እንዲያው ተቸገርሽ እኔስ አይገርመኝም ወዶ መጥላትሽ ጥለሽኝ ብትሔጂ ካልከበደሽ ግፉ አላስገድድሽም ትዝብት ነው ትርፉ ጥንትም ላይሆንልሽ እንዲያው ተቸገርሽ እኔስ አይገርመኝም ወዶ መጥላትሽ ጥለሽኝ ብትሔጂ ካልከበደሽ ግፉ አላስገድድሽም ትዝብት ነው ትርፉ ፍቅርም ካልቀደመ ከገንዘብ ከሓብቱ ቁምነገር የለውም መዋደድ በከንቱ ካንቺማል ደብቀው ችዬ ማልሸሽግሽ መውደዴን ነው እኔ መቼም የማልነጥቅሽ በአይኔ ሳይሰሰት በእጄም ሳልነጥለው የማላውቀው ልብሽ ምንግዜም ፍቅሬ ነው ቢከብድም ባይከብድም በምድር ውለታዬ ላንቺ የማቀርበው ይህ ነው ስጦታዬ ቁምነገር ነው ብዬ ውለታን ውያለው አላስቀየምኩሽም ቃሌን አክብሬያለው በደል ከቁምነገር ከበዛብሽማ አቻሽን ፈልጊ ላንቺ እንደሚስማማ በደል ከቁምነገር ከበዛብሽማ አቻሽን ፈልጊ ላንቺ እንደሚስማማ ጥንትም ላይሆንልሽ እንዲያው ተቸገርሽ እኔስ አይገርመኝም ወዶ መጥላትሽ ጥለሽኝ ብትሔጂ ካልከበደሽ ግፉ አላስገድድሽም ትዝብት ነው ትርፉ ጥንትም ላይሆንልሽ እንዲያው ተቸገርሽ እኔስ አይገርመኝም ወዶ መጥላትሽ ጥለሽኝ ብትሔጂ ካልከበደሽ ግፉ አላስገድድሽም ትዝብት ነው ትርፉ አንዱ ብሩን ሲቸር ሌላው ከየት ያመጣል የኔ ልብ ሐብታም ነው እምነቱን ይሰጣል ዛሬም አለኝ ፍቅር የያዝኩት ሰስቼ መቼም በዚህ በኩል አላውቅም ደህይቼ ጎጆማ ጓዳማ ቤትማ ነበረኝ ማዕድ የሚያቋርስ ሰው ነው የቸገረኝ ዛሬ እኔን ዘንግቶ ገላሽ ሰው ቢለምድም ትላንት ወደሽኛል ክፉሽን አልፈቅድም ቁምነገር ነው ብዬ ውለታን ውያለው አላስቀየምኩሽም ቃሌን አክብሬያለው በደል ከቁምነገር ከበዛብሽማ አቻሽን ፈልጊ ላንቺ እንደሚስማማ በደል ከቁምነገር ከበዛብሽማ አቻሽን ፈልጊ ላንቺ እንደሚስማማ ጸጸቱ እስኪሰማሽ ጨክኔሽ ብትቆርጪ ለኔው ይብላኝ እንጂ አንቺስ ሰው አታጪ ይሻል ይሁን ብለሽ ከተነሳሽ አንቺ እኔም ሸኝቻለሁ በይ ደህና ሰንብቺ ይሻል ይሁን ብለሽ ከተነሳሽ አንቺ እኔም ሸኝቻለሁ በይ ደህና ሰንብብቺ የህልምሽ ሎተሪ ቅዠት ነው አይወጣም ይባስ ይሁን እንጂ የተሻለ አይመጣም ገንዘብ ከሰው በልጦ ከጠቀመሽ ላንቺ አላስገድድሽም በይ ደህና ሰንብቺ ገንዘብ ከሰው በልጦ ከጠቀመሽ ላንቺ አላስገድድሽም በይ ደህና ሰንብቺ
Writer(s): Elias Woldemariam, Yilma G/ab Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out