Lyrics

ልቤ መሸነፉን እንዳይነግራት ሰጋ ወራቱም አለፈ ክረምትና በጋ የሆዴን መጨነቅ ፍቅሬ መች ገባት ትስቃለች እሷ ልጅነት ይዟት ልቤ መሸነፉን እንዳይነግራት ሰጋ ወራቱም አለፈ ክረምትና በጋ የሆዴን መጨነቅ ፍቅሬ መች ገባት ትስቃለች እሷ ልጅነት ይዟት በውበት ቁንጅና መልኳ መች አነሰ ቀርቤ እንዳልነግራት ልጅነቷ ባሰ የሆዴ መጨነቅ ባይገባት ነው ለሷ ቀርቤ ስነግራት የሚስቀው ጥርሷ ልቤ መሸነፉን እንዳይነግራት ሰጋ ወራቱም አለፈ ክረምትና በጋ የሆዴ መጨነቅ ፍቅሬ መች ገባት ትስቃለች እሷ ልጅነት ይዟት ተይ አስታሚው መራቅሽ ይቅር ግፍ አትስሪ ጡር አለው ፍቅር እንደሰት ልርሳሽ ከሆዴ አውጥቼ ባይንሽ ውበት እዳ ገብቼ እዳ ገብቼ እዳ ገብቼ አስረሽኛል አልሠዎስም እስቲ ፍቺኝ በይ እንደ ቄስ እንዳልከስሽ ለመሪ፟ጌታ ከልጅ ውሎ የለም ስሞታ የለም ስሞታ የለም ስሞታ ልቤ መሸነፉን እንዳይነግራት ሰጋ ወራቱም አለፈ ክረምትና በጋ የሆዴን መጨነቅ ፍቅሬ መች ገባት ትስቃለች እሷ ልጅነት ይዟት ልቤ መሸነፉን እንዳይነገሸራት ሰጋ ወራቱም አለፈ ክረምትና በጋ የሆዴን መጨነቅ ፍቅሬ መች ገባት ትስቃለች እሷ ልጅነት ይዟት ልነግራት እልና ነገ ዛሬ እያልኩኝ የፍቅርን እረመጥ አዝዬው ከረምኩኝ ሆዴ ላይሆንለት እንዲያው ተጨነቀ ሁኔታዋ ሁሉ ነብስ እንዳላዎቀ ልቤ መሸነፉን እንዳይነግራት ሰጋ ወራቱም አለፈ ክረምትና በጋ የሆዴን መጨነቅ ፍቅሬ መች ገባት ትስቃለች እሷ ልጅነት ይዟት አሳምሮ ውበት ቢያድላት ፍቅር አታውቅም ልጅነት አላት ተመኝቼው ድንቅ ውበቷን እንዴት ላርገው ልጅነቷን ልጅነቷን ልጅነቷን ቀድማ ስቃ ቀልቤን ገዛችው ልቤን ማርካ ደጅ አስጠናችው ወይ አትደግፈኝ አዝና ለነብሷ ትስቃለች ተይዤ በሷ ተይዤ በሷ ተይዤ በሷ አሳምሮ ውበት ቢያድላት ፍቅር አታውቅም ልጅነት አላት ልጅነት አላት ልጅነት አላት ተመኝቼው ድንቅ ውበቷን እንዴት ላርገው ልጅነቷን ልጅነቷን ልጅነቷን
Writer(s): Teddy Afro Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out