Lyrics

በመንታ ጡቶቻ መሃል ተጋድሜ በጥርሷ ዘበኛ በከንፈር ታድሜ ስነቃ ባዶ ቤት ናፍቆት ተሸልሜ ላላገኛት ነውወይ ላይፈታ ህልሜ ላላገኛት ነውወይ ይሄሁሉ ህልሜ በጥርሷ ዘበኛ በከንፈር ተድሜ ጡቶቻ መሃል ስኖር ተጋድሜ ስነቃ ባዶ ቤት ናፍቆት ተሸልሜ ላላገኛት ነውወይ ላይፈታ ህልሜ ላላገኛት ነውወይ ይሄሁሉ ህልሜ Instrumental እንዴት ያስደስታል ፍቅር በህልም አፍ ገጥሞ ጨዋታ ሲያስለመልም ጽድቅ ነበር በዛው ቢሉ ጭልም ምኞት ባጥቢያ ዳኛ ላይታገድ በህልም አለም ጉዞ በሃሳብ መንገድ ሌሊት መባከን ይሻል ከአጉል መውደድ ሀገሯ ወዲያ ማዶ ሀገሯ ወዲያ ማዶ ሀገሯ ወዲያ ማዶ ናፍቆቷ መጣ ማልዶ ሀገሯ ወዲያ ማዶ ሀገሯ ወዲያ ማዶ ሀገሯ ወዲያ ማዶ ናፍቆቷ መጣ ማልዶ Instrumental ስጋጃ አንጥፌ ግምጃ ብጋርድ እንኳን ሊሞቀኝ አለኝ ብርድ ብርድ ጤዛ ወሮታል የኛውን ሰፈር ብቻን መኝታ እንደምን ልድፈር ሌት ፈሌት ለመንገድ ቀን ከመሰወር ምነው እንደ አጥቢያ ብትወረወር Instrumental አይሆንላት ይሆን ከዐይን መሰወሯ በህልም እንደሸማኔ ፍቅር መደወሯ የአንድአንዱ ሰው ጥበብ ምኑ ይታወቃል ቀን እያስቀደሰ ሌሊት ልብ ይሰርቃል ቀን እያስቀደሰ ሌሊት ልብ ይሰርቃል ደግሞ መሸ መሸ እስኪላነጣጥፈው ቀኑን እየባንነኩ ሌሊቱን በሃሳብ ባልፈው የእንቅልፍ አጀብ ከብዶኝ በሰመመን ስናኝ በህልሜ ትመጣለች ያቺ የቀን መናኝ በህልሜ ትመጣለች ያቺ የቀን መናኝ አሄሄ ሀገሩ የት ይሆን የዋልሺበት ታሳድሪ እንደሆን የመሸበት ጠያይቄ ልምጣ ካለሽበት በፍቅር እያሰብኳት ከመብሰልሰል ሌሊት እያሰብኳት ከምደሰት ነግቶ ባያት ምነው ብትከሰት ሀገሯ ወዲያ ማዶ ሀገሯ ወዲያ ማዶ ሀገሯ ወዲያ ማዶ ናፍቆቷ መጣ ማልዶ ሀገሯ ወዲያ ማዶ ሀገሯ ወዲያ ማዶ ሀገሯ ወዲያ ማዶ ናፍቆቷ መጣ ማልዶ Instrumental አይችሉም እንጂ ብቸኝነቴን እንደምን ልጣት ፍቅሬን እምነቴን ባይልላት ነው ወይ ባይልልኝ እሷ አይቆርጥላት እኔ አይለይልኝ ከሆድ ላትወጣ አወይ መቸገር አንጀት ስትበላ የደሃ ነገር አንጀት ስትበላ የደሃ ነገር አንጀት ስትበላ የደሃ ነገር አንጀት ስትበላ የደሃ ነገር አንጀት ስትበላ አንጀት ስትበላ የደሃ ነገር
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out