Credits
PERFORMING ARTISTS
Abeba Desalenge
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Samuel Tadesse
Songwriter
Lyrics
እስቲ ልጠይቅህ ንገረኝ ስሜትክን
ምን እንደተሰማህ ስቀር በፍቅርህን
ሄደህ ወደኋላ ተመልሰህ ለአፍታ
አስታዉሰህ ንገረኝ ያችን ቅፅበት ብቻ
ላስብበት ብዬ ስመልስህ እኔ
ትተኸዉ እንዳትቀር ይቅር ነስቶህ ወኔ
ይሆናል አይሆንም ሁለት ልብ ተከፍሎ
ለፍቅርህ ስስማማ ምን ተሰማህ አንተ
ማንም በሌለበት እኔና አንተ ብቻ
የፍቅር መሰዋት ልትሰዋ ስትመጣ
በሀዘንና ደስታ ተሞልቶ ገፅታ
ምን ተሰማህ አንተ እሽ የልኩህ ለታ
ማንም በሌለበት እኔና አንተ ብቻ
የፍቅር መሰዋት ልትሰዋ ስትመጣ
በሀዘንና ደስታ ተሞልቶ ገፅታ
ምን ተሰማህ አንተ እሽ የልኩህ ለታ
አይኖቼን እያየህ በጉጉት ነ,በስጋት
ሆድህ ባር ባር ሲለዉ መልሴን ስትናፍቃት
ምን እንደተሰማህ ንገረኝ በሞቴ
እሺ የሚለዉን ቃል ሲያወጣ አንደበቴ
ፊት እየነሳሁህ የገባኸኝ መሽዬ
ከቶ ምን ተረዳህ ሲመጣ እሽታዬ
ችለህ ስትጠብቀኝ መልሴን ናፍቆ ጆሮህ
ምን ትለኝ ነበረ እምቢ ብልህ ኖሮ
እንቅልፍ እንደሌለህ ደጋግመህ ስትነግረኝ
ሀሳብህ እንደሆንኩ ሰርክ ስታስረዳኝ
መልሴን ሳዘገየዉ እያልኩ ነገ ዛሬ
እሽ ባልኩህ ሰዓት ምን ተሰማህ ፍቅሬ
እንቅልፍ እንደሌለህ ደጋግመህ ስትነግረኝ
ሀሳብህ እንደሆንኩ ሰርክ ስታስረዳኝ
መልሴን ሳዘገየዉ እያልኩ ነገ ዛሬ
እሽ ባልኩህ ሰዓት ምን ተሰማህ ፍቅሬ
Writer(s): Elias Woldemariam, Samuel Tadesse
Lyrics powered by www.musixmatch.com