Lyrics

ከተመኘሁትም ካለምኩትም በላይ ፍቅር አለ በህይወቴ ሁሉም አንተን በማግኘቴ ከታገልኩለትም ከጣርኩትም በላይ ደስተኛ ነኝ በህይወቴ ሁሉም አንቺን በማግኘቴ የኔ ቆንጆ ዉብ እኮ ነህ የታላቅ ጥበብ ትዕይንት የኔ ቆንጆ የምታምር ልዩ ስራ ግሩም ፍጥረት እወድሃለሁ መቼም ቢሆን አንተ ለኔ ነህ ልዩ ሰው እወድሃለሁ ዛሬም ነገም አለውጥህም በምንም የኔ ቆንጆ የኔ ቆንጆ የኔ ቆንጆ የኔ ቆንጆ ተስፋ ካደረኩት ከልቤ እምነት በላይ እውነት አየሁ በኛ ፍቅር አንቺን ሰጠኝ እሱ ይክበር ከሰማሁት ከጠበኩት በላይ ሰላም አለ በኛ ፍቅር አንተን ሰጠኝ እሱ ይክበር የኔ ቆንጆ የነፍሴ አጋር የእውነት ደስታን አፍላቂዬ የኔ ቆንጆ ድንቅ ታእምር አምላኬን ማመስገኛዬ እወድሻለሁ መቼም ቢሆን አንቺ ለኔ ነሽ ልዩ ሰው እወድሻለሁ ዛሬም ነገም አለዉጥሽም በምንም የኔ ቆንጆ የኔ ቆንጆ የኔ ቆንጆ (የኔ ቆንጆ) ድንቅ ታእምር (የኔ ቆንጆ) አምላኬን ማመስገኛዬ እወድሃለሁ መቼም ቢሆን አንተ ለኔ ነህ ልዩ ሰው እወድሃለሁ ዛሬም ነገም አለዉጥህም በምንም
Writer(s): Samuel Alemu, Eyob Mekonen Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out