Lyrics

እስኪ ማን ማን ሊወደድ ካንቺ እኩል ሚዛን ደፍቶ ሲያዩትም ያላማረ ቢበላም አይጥም ከቶ ከሰው መቆለል ሹመት ከዛፍም ያለው ጥላ ይባላል ደሞም የለም ተወዳጅ ካንቺ ሌላ (ደሞ ሌላ) አለ ወይ ካንቺ ሌላ (ደሞ ሌላ) በፍቅር የተሞላ (ደሞ ሌላ) አይኔ ቢያይ ሌላ ውበት (ደሞ ሌላ) ልቤማ አንቺ አለሽበት ስንት አልፎ ደክሞ ነው (ልቤ) ልብሽ ጋር የደረሰው አፈር ዘግኖ ምሏል (መቼም) ላይለምድ ከሌላ ሰው ሚስጥሩ ምንድነው (ብዬ) እራሴን ብጠይቀው መልሱን ይሰጠኛል (ፍቅርሽ) ውስጤን እስከሚደንቀው እንደ ደራሽ እስኪያጥለቀልቀኝ ያንቺ መውደድ እኔን ያስጨንቀኝ እንደ ደራሽ እስኪያጥለቀልቀኝ ያንቺ መውደድ እኔን ያስጨንቀኝ (ደሞ ሌላ) አለ ወይ ካንቺ ሌላ (ደሞ ሌላ) በፍቅር የተሞላ (ደሞ ሌላ) አይኔ ቢያይ ሌላ ውበት (ደሞ ሌላ) ልቤማ አንቺ አለሽበት እስኪ ማን ማን ሊወደድ ካንቺ እኩል ሚዛን ደፍቶ ሲያዩትም ያላማረ ቢበላም አይጥም ከቶ ከሰው መቆለል ሹመት ከዛፍም ያለው ጥላ ይባላል ደሞም የለም ተወዳጅ ካንቺ ሌላ (ደሞ ሌላ) አለ ወይ ካንቺ ሌላ (ደሞ ሌላ) በፍቅር የተሞላ (ደሞ ሌላ) አይኔ ቢያይ ሌላ ውበት (ደሞ ሌላ) ልቤማ አንቺ አለሽበት ያሁኑ ደስታዬን (ሳስብ) ያጓጓኛል የነገው ካለሽኝ አልሰጋም (ውዴ) ቢሆንም የፈለገው እምቢ ብዬ አላውቅም (ሆዴ) ለመጣ ወይ ለሄደው አልነበረምና (ለኔ) እንዳንቺ የምወደው እንደ ደራሽ እስኪያጥለቀልቀኝ ያንቺ መውደድ እኔን ያስጨንቀኝ እንደ ደራሽ እስኪያጥለቀልቀኝ ያንቺ መውደድ እኔን ያስጨንቀኝ (ደሞ ሌላ) አለ ወይ ካንቺ ሌላ (ደሞ ሌላ) በፍቅር የተሞላ (ደሞ ሌላ) አይኔ ቢያይ ሌላ ውበት (ደሞ ሌላ) ልቤማ አንቺ አለሽበት (ደሞ ሌላ) አለ ወይ ካንቺ ሌላ (ደሞ ሌላ) በፍቅር የተሞላ (ደሞ ሌላ) አይኔ ቢያይ ሌላ ውበት (ደሞ ሌላ) ልቤማ አንቺ አለሽበት (ደሞ ሌላ) አለ ወይ ካንቺ ሌላ (ደሞ ሌላ) በፍቅር የተሞላ (ደሞ ሌላ) አይኔ ቢያይ ሌላ ውበት
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out