Lyrics

አደብ ግዛ ልቤ ሆዴም ተው አይባስህ መጨከንም ልመድ ላይቀር መለየትህ መበርታት ነው እንጂ የምን ሀዘን ማብዛት በኔ አልተጀመረም አፍቅሮ ሰው ማጣት አደብ ግዛ ልቤ ሆዴም ተው አይባስህ መጨከንም ልመድ ላይቀር መለየትህ መበርታት ነዉ እንጂ የምን ሀዘን ማብዛት በኔ አልተጀመረም አፍቅሮ ሰው ማጣት አይ እኔማ ሁሉን ችዬ ኖርኩኝ መለየቱ ከብዶኝ አይ እኔማ ታዲያ እስከቼ ነው እሷን ማለት ቆርጦ አይ እኔማ ከመሰላት ትሁን ትራቀኝ ትለየኝ አይ እኔማ ብቻ የሷን ክፉ ፈፅሞ አያሳየኝ አብሮ መኖር ነው የኔ አለም የሚበጀን መለየትማ ሆድዬ ምን ሊጠቅመን አንዱን ቢለዩት አንዱ ይመጣል ፍቅር ጣጣው መቼ እንዲህ ያልቃል አብሮ መኖር ነው የኔ አለም የሚበጀን መለየትማ ሆድዬ ምን ሊጠቅመን አንዱን ቢለዩት በአንዱ ይመጣል ፍቅር ጣጣው መቼ እንዲህ ያልቃል አንዱን ቢለዩት በአንዱ ይመጣል ፍቅር ጣጣው መቼ እንዲህ ያልቃል አደብ ግዛ ልቤ ሆዴም ተው አይባስህ መጨከንም ልመድ ላይቀር መለየትህ መበርታት ነው እንጂ የምን ሀዘን ማብዛት በኔ አልተጀመረም አፍቅሮ ሰው ማጣት አደብ ግዛ ልቤ ሆዴም ተው አይባስህ መጨከንም ልመድ ላይቀር መለየትህ መበርታት ነው እንጂ የምን ሀዘን ማብዛት በኔ አልተጀመረም አፍቅሮ ሰው ማጣት አሄ እኔማ ሰው ወዶ መለየት እድሌ ከሆነ አሄ እኔማ ምነው ልቤ ረስቷት ከሀሳቡ በዳነ አሄ እኔማ ዋ ብዬ ብቀርም ናፍቆቷን ታቅፌ አሄ እኔማ ለእሷም ይቅናት እስኪ ክፉ አይወጣም ከአፌ አብሮ መኖር ነው የኔ አለም የሚበጀን መለየትማ ሆድዬ ምን ሊጠቅመን አንዱን ቢለዩት በአንዱ ይመጣል ፍቅር ጣጣው መቼ እንዲህ ያልቃል አብሮ መኖር ነው የኔ አለም የሚበጀን መለየትማ ሆድዬ ምን ሊጠቅመን አንዱን ቢለዩት በአንዱ ይመጣል ፍቅር ጣጣው መቼ እንዲህ ያልቃል አንዱን ቢለዩት በአንዱ ይመጣል ፍቅር ጣጣው መቼ እንዲህ ያልቃል አንዱን ቢለዩት በአንዱ ይመጣል ፍቅር ጣጣው መቼ እንዲህ ያልቃል አንዱን ቢለዩት በአንዱ ይመጣል ፍቅር ጣጣው መቼ እንዲህ ያልቃል
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out