Lyrics

የጀግና ልጅ የዛ ኩሩ የጎበዝ ልጅ ከሰሜን ከደቡብ ከምዕራብ ከምስራቅ ስንት አለ ጎበዝ ቢጠራ ማያልቅ ከሰሜን ከደቡብ ከምዕራብ ከምስራቅ ስንት አለ ጎበዝ ቢጠራ ማያልቅ ሀገር ሀገር ሀገር ኧረ እናት ሀገሬ ሀገር ሀገር ሀገር ኧረ ኢትዮጲያ ሀገሬ ሀገር ሀገር ሀገር ኧረ እማማ ሀገሬ ሀገር ሀገር ሀገር ኧረ እናት ሀገሬ የጀግና ልጅ የዛ ኩሩ ዓይን አለው ወይ ምንሽሩ እንደ ፀሀይ እንደ ቀትር እኩል በእኩል የሚመትር ለወደደው ከመደቡ ለጠላው ሰው ከወገቡ ወንድነቱን ማን አየበት ዝናሩ ነው የዞረበት ቴዎድሮስ ለአንድነቷ በሞቱ ሲፀነስ አንገቱን ሰጥቶ ነው ያጸናት ዩሃንስ ካሳ አንድ ለእናቱ አትበሉኝ አልወድም ከገብርዬው በላይ ከየት ይመጣል ወንድም አያስቡሽ እንጂ በክፉ አንቺን ብቻ ሺህ ገበየሁ ቢሞት አለ በሉ ባልቻ ፈትሉ በወርቅ ሽመና በልክ ሀገሬ አጠብም ተሰፍታ በልክ ሀገር ሀገር ሀገር ከሰሜን ከደቡብ ከምዕራብ ከምስራቅ ስንት አለ ጎበዝ ቢጠራ ማያልቅ ከሰሜን ከደቡብ ከምዕራብ ከምስራቅ ስንት አለ ጎበዝ ቢጠራ ማያልቅ ጥራ አባ ጅፋር የወንዶቹን ቁና ለጠላቱ ይሳቅ ለወደደው ቡና እኔ የሀበሻ ልጅ የዛ ንጉስ ጦና ጀግናን ማወዳደስ ይቀረናል ገና በገበየው ባርኮት ሊቁ ሀብተጊዮርጊስ ኸረ እንዴት አማረ የአድዋ ላይ ድግስ ገበየሁን ጥሩት በሉት አባጎራው በፈረሱ ሲሄድ ሽለላ ፉከራው ቆየኝ አንዴ እዛ ጋር ስማ የራስ ሚካኤል እጅ የነ ራስ መንገሻ ለጠላት አያጣም ጥጋብ ማስታገሻ አላሚ ሰው ሲገኝ እንደ አበበ አረጋይ በመሬት ያስኬዳል በራሪን እንደ ድንጋይ ሊቀመኳስ ነው ወይ አባተጓ ያለው መድፉን ከአፈሩ ምን የቀላቀለው እንደ ራስ ተፈሪ ስም አጣ ምላሴ መቀባት እንዲህ ነው ሀይልን ከስላሴ በላይ በላይ ብዬ ሳስበው እጅጉን ፎክር ይላል ልቤ አንስተህ በእልጅጉን የዞማን በረሃ ዝናቡ ሲፈራው ደሙን አይደል እንዴ ያጠጣው ሽፈራው ሀገር ሀገር ሀገር ኧረ እናት ሀገሬ ሀገር ሀገር ሀገር ኧረ ኢትዮጲያ ሀገሬ ሀገር ሀገር ሀገር ኧረ እማማ ሀገሬ ሀገር ሀገር ሀገር ኧረ እናት ሀገሬ ኧረ እናት ሀገሬ ኧረ ኢትዮጲያ ሀገሬ ኧረ እማማ ሀገሬ ኧረ እናት ሀገሬ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out