Lyrics

ካምናው ካልተማርኩኝ ተመልሼ እኔም ዛሬም ከደገመኝ እርምን አላቅ ብዬ እንደገና አዬ ሰው ማመን ካመመኝ አሀ ሞኙ ልቤ አሀ ያልተደለ አሀ ምን ሊፈይድ ከታለለ የካብኩት ተናደ ባለማወቅ ስገነባው ፈርሶ ባፀዳው ቆሸሸ እንደገና የፀዳው ደፍርሶ ወርቅ አይደለ ነገር አይጣራ በእሳት አልፈትሸው የቸገረ ነገር ግራ ገባኝ በምን ይለያል ሰው ቀድሞ አለመጠንቀቅ ጥንቱን አለመፍራት ሀይለኛ ዱላ ነው ያረፈብኝ ማገገሜን እንጃ ምን ተሻለኝ እንደማንገናኝ ልቤ እያወቀው አፍቅሮ መለየት መንፈሴን ጨነቀው አንቺም ላታገኚኝ እኔም ያንቺ ላልሆን ያለመረሳትሽ ምስጢሩ ምን ይሆን ካምናው ካልተማርኩኝ ተመልሼ እኔም ዛሬም ከደገመኝ እርምን አላቅ ብዬ እንደገና አዬ ሰው ማመን ካመመኝ አሀ ሞኙ ልቤ አሀ ያልታደለ አሀ ምን ሊፈይድ አሀ ከታለለ መቁረጥ ከተሳነኝ ምን ይደረግ አውቆ እንዳላወቀ ይበለው ምናለ ልቤንማ ዳግም ከወደቀ ቁስሌም ላይጠገን የበፊቱ ጠባሳዉ ላይጠፋ ከተመለስክበት ሞኙ ልቤ በል እንግዲህ ልፋ በትካዜ ብሩሽ በሀሳብ ሸራ ላይ ስስል ከረምኩና ሳሳምርሽ ህልም እልም ሆንሽና ዛሬም የለሽ እንደማንገናኝ ልቤ እያወቀው አፍቅሮ መለየት መንፈሴን ጨነቀው አንቺም ላታገኚኝ እኔም ያንቺ ላልሆን ያለመረሣትሽ ምስጢሩ ምን ይሆን አሀ ሞኙ ልቤ አሀ ያልታደለ አሀ ምን ሊፈይድ አሀ ከታለለ...
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out