Top Songs By Madingo Afework
Similar Songs
Lyrics
ካምናው ካልተማርኩኝ ተመልሼ
እኔም ዛሬም ከደገመኝ
እርምን አላቅ ብዬ እንደገና
አዬ ሰው ማመን ካመመኝ
አሀ ሞኙ ልቤ አሀ ያልተደለ
አሀ ምን ሊፈይድ ከታለለ
የካብኩት ተናደ ባለማወቅ ስገነባው ፈርሶ
ባፀዳው ቆሸሸ እንደገና የፀዳው ደፍርሶ
ወርቅ አይደለ ነገር አይጣራ በእሳት አልፈትሸው
የቸገረ ነገር ግራ ገባኝ በምን ይለያል ሰው
ቀድሞ አለመጠንቀቅ ጥንቱን አለመፍራት
ሀይለኛ ዱላ ነው ያረፈብኝ
ማገገሜን እንጃ ምን ተሻለኝ
እንደማንገናኝ ልቤ እያወቀው
አፍቅሮ መለየት መንፈሴን ጨነቀው
አንቺም ላታገኚኝ እኔም ያንቺ ላልሆን
ያለመረሳትሽ ምስጢሩ ምን ይሆን
ካምናው ካልተማርኩኝ ተመልሼ እኔም ዛሬም ከደገመኝ
እርምን አላቅ ብዬ እንደገና አዬ ሰው ማመን ካመመኝ
አሀ ሞኙ ልቤ አሀ ያልታደለ
አሀ ምን ሊፈይድ አሀ ከታለለ
መቁረጥ ከተሳነኝ ምን ይደረግ አውቆ እንዳላወቀ
ይበለው ምናለ ልቤንማ ዳግም ከወደቀ
ቁስሌም ላይጠገን የበፊቱ ጠባሳዉ ላይጠፋ
ከተመለስክበት ሞኙ ልቤ በል እንግዲህ ልፋ
በትካዜ ብሩሽ በሀሳብ ሸራ ላይ
ስስል ከረምኩና ሳሳምርሽ
ህልም እልም ሆንሽና ዛሬም የለሽ
እንደማንገናኝ ልቤ እያወቀው
አፍቅሮ መለየት መንፈሴን ጨነቀው
አንቺም ላታገኚኝ እኔም ያንቺ ላልሆን
ያለመረሣትሽ ምስጢሩ ምን ይሆን
አሀ ሞኙ ልቤ አሀ ያልታደለ
አሀ ምን ሊፈይድ አሀ ከታለለ...
Lyrics powered by www.musixmatch.com