Lyrics

ውሰጂያት ውሰጂያት ነፍሴን በስጦታ ሽልማት እንድትሆን ላንቺ ተበርክታ ስለሚበልጥብኝ ከኔ የሷ ደስታ ነፍሴን እንቺ አልኳት ስለሚበልጥብኝ ከኔ የሷ ደስታ ነፍሴን እንቺ አልኳት ቃልሽን አድምጬ በመኖሬ ቃሌን በመስማትሽ ከገላዬም በላይ እስትንፋሴ ትሁን ሽልማትሽ ፍቅር ቸር ማድረጉ በኛ ታይቶ ታምኖ ተከበረ ሰውን የሚያሳሳው ከነፍስ ወዲያ ሌላ ምን ነበረ ውሰጂያት እንግዲህ ውሰጂያት ብያለው ህይወቴን ልሰጥሽ ተዘጋጅቻለው አንቺን የጣለልኝ ቸሩ አምላኬ ይክበር ለኔ ባይልልኝ የት አገኝሽ ነበር ውሰጂያት ውሰጂያት ነፍሴን በስጦታ ሽልማት እንድትሆን ላንቺ ተበርክታ ስለሚበልጥብኝ ከኔ የሷ ደስታ ነፍሴን እንቺ አልኳታ ስለሚበልጥብኝ ከኔ የሷ ደስታ ነፍሴን እንቺ አልኳት ፍጹም ጨዋነትሽን ተመልክቼ ላክብርሽ ማለቴ ደጋግሜው እንጂ ጥሩነትሽን መች በአንዴ ሁለቴ እኔ ለውለታሽ በሽልማት ነፍሴን ብሰጥሽም በመናገር እንጂ በማስተዋል አንቺን አልበልጥሽም ስትሄጃት እንደኖርሽ ስኖር አይቻለው ህይወቴን ልሰጥሽ ተዘጋጅቻለው ለምኛት እንዳንቺ ማናት የገዛችኝ እንቁም ብሩም አንሷት ህይወት ያሰጠችኝ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out