Lyrics

አባት ፡ አለኝ ፡ አባት ሁል ፡ ጊዜ ፡ የምመካበት ሚረዳኝ ፡ ሚራራልኝ ከጐኔ ፡ የማይለየኝ ምሕረቱ ፡ የበዛ ፡ በሕይወቴ ያሳደገኝ ፡ ከልጅነቴ እኔ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ነኝ ምሕረቱ ፡ ያቆመኝ አይተኛም ፡ እርሱ ፡ እኔን ፡ እየጠበቀ ከክፉ ፡ አውሬ ፡ እየተናጠቀ ያሳድረኛል ፡ በለምለሙ ፡ ስፍራ በእጆቹ ፡ ይዞኛል ፡ ክፉን ፡ እንዳልፈራ ላምልክህ ፡ ወድጄ ፡ እጆቼን ፡ አንስቼ መልካምነትህ ፡ አይተዋል ፡ ዓይኖቼ ውሰድ ፡ አምልኮዬን ፡ መስዋዕቴን ዛሬም ፡ አይሰለቸኝ ፡ አንተን ፡ ማመስገን የወደቀውን ፡ ሰው ፡ አንስቶ አስውቦ ፡ ታሪኩን ፡ ለውጦ በምሕረትህ ፡ ቆሞ ፡ እንደገና ይዞ ፡ መጥቷል ፡ በዙ ፡ ምሥጋና ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ ፡ ባለውለታዬ ፡ ክበር ፡ እግዚአብሔር አባት ፡ አለኝ ፡ አባት ሁል ፡ ጊዜ ፡ የምመካበት ሚረዳኝ ፡ ሚራራልኝ ከጐኔ ፡ የማይለየኝ ምሕረቱ ፡ የበዛ ፡ በሕይወቴ ያሳደገኝ ፡ ከልጅነቴ እኔ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ነኝ ምሕረቱ ፡ ያቆመኝ የደከመውን ፡ በፍቅር ፡ ሚያነሳ ሰው ፡ የረሳውን ፡ ከቶ ፡ የማይረሳ ይቅርታው ፡ ብዙ ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አይፈርድ እውነተኛ ፡ አባት ፡ ልጆቹን ፡ ሚወድ ላምልክህ ፡ ወድጄ ፡ እጆቼን ፡ አንስቼ መልካምነትህ ፡ አይተዋል ፡ ዓይኖቼ ውሰድ ፡ አምልኮዬን ፡ መስዋዕቴን ዛሬም ፡ አይሰለቸኝ ፡ አንተን ፡ ማመስገን የወደቀውን ፡ ሰው ፡ አንስቶ አስውቦ ፡ ታሪኩን ፡ ለውጦ በምሕረትህ ፡ ቆሞ ፡ እንደገና ይዞ ፡ መጥቷል ፡ በዙ ፡ ምሥጋና ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ልበልህ ፡ ባለውለታዬ ፡ ክበር ፡ እግዚአብሔር
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out