Lyrics

አያይዘን ፡ አንድ ፡ አድርገን እንዳንጠፋ ፡ ተነካክሰን አያይዘን ፡ አንድ ፡ አድርገን እንዳንጠፋ ፡ ተነካክሰን ቃየን ፡ ወንድሙን ፡ ገደል ጌታ ፡ መስዋዕቱን ፡ ስላልተቀበለ ልቡ ፡ በቅናት ፡ ተሞልቶ ለጥፋት ፡ ተነሳ ፡ ጭካኔ ፡ ተሞልቶ ዛሬም ፡ እንደ ፡ ቃየን ፡ አለ ፡ እንደገና ለምን ፡ ተሳካለት ፡ ብሎ ፡ የሚቀና ሰይፍ ፡ ይዟል ፡ በእጁ ፡ አፉ ፡ እንደማር ጉድጓድ ፡ ይቆፍራል ፡ ገድሎ ፡ ሊቀብር አያይዘን ፡ አንድ ፡ አድርገን እንዳንጠፋ ፡ ተነካክሰን ከሁሉ ፡ መጀመሪያ ፡ የታዘዝኩት ፡ ፈቃድ እንኳን ፡ ወንድሚንና ፡ ጠላቴን ፡ እንድወድ እጃችን ፡ ተያይዞ ፡ ልባችን ፡ ተራራቀ ከየት ፡ ፈውስ ፡ ይመጣል ፡ መርዙ ፡ ከተደበቅ አያይዘን ፡ አንድ ፡ አድርገን እንዳንጠፋ ፡ ተነካክሰን በቤትህ ፡ ውድድሩ ፡ በዛ እኔ ፡ ልታይ ፡ ልታይ ፡ እኔ ፡ ብቻ ፡ ልግዛ ቃልህን ፡ የሚሰብከው ፡ ሞልቶ እንደሚናገረው ፡ ይሚኖረው ፡ ጠፍቶ ነብይ ፡ አስተማሪ ፡ ሁሉ ፡ ጐራ ፡ ይዞ ሰይፍ ፡ ይማዘዛል ፡ እዛ ፡ እዚህ ፡ ማዶ አካል ፡ ተበታትኖ ፡ ዓይኖረውም ፡ ውበት ማን ፡ ክብርህን ፡ ወስዶ ፡ ይኖራል ፡ በሕይወት አያይዘን ፡ አንድ ፡ አድርገን እንዳንጠፋ ፡ ተነካክሰን ከሁሉ ፡ መጀመሪያ ፡ የታዘዝኩት ፡ ፈቃድ እንኳን ፡ ወንድሚንና ፡ ጠላቴን ፡ እንድወድ እጃችን ፡ ተያይዞ ፡ ልባችን ፡ ተራራቀ ከየት ፡ ፈውስ ፡ ይመጣል ፡ መርዙ ፡ ከተደበቅ የህግ ፡ ሁሉ ፡ ፍጻሜ ፡ የትዛዛትም ፡ ሁሉ ፡ መጀመሪያ ባልንጀራህን ፡ እንደ ፡ እራስህ ፡ አድርገህ ፡ ውደድ ፡ ብለኸን የቤትህ ፡ ማገርና ፡ መሰሶ ፡ የሆነውን ፡ ፍቅርን ፡ ጥለን ፍቅርን ፡ ስንገፋት ፡ ስትወጣ ፡ ከቤቷ እግሯን ፡ ተከትሎ ፡ ገባ ፡ ያ ፡ ጠላቷ ማናከስ ፡ ጀመረ ፡ እንድንጠፋፋ አደባባይ ፡ ወጥተን ፡ እንድንገፋፋ ሰው ፡ አካሉን ፡ መብላት ፡ መንከስ ፡ ከጀመረ መገመት ፡ ይቻላል ፡ ምን ፡ ሊሆን ፡ እንዳለ አወይ ፡ ጉድ ፡ ሆነናል ፡ ወገን ፡ ተው ፡ እንንቃ ፍቅር ፡ በሊለበት ፡ እርሱም ፡ የለም ፡ ለካ አያይዘን ፡ አንድ ፡ አድርገን እንዳንጠፋ ፡ ተነካክሰን
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out