Lyrics

ሚነጋ ፡ አይመስልም ፡ ሌሊቱ ፡ ረዝሞ ጨለማውን ፡ አይቶ ሌሊቱም ፡ ያልፋል ፡ ደግሞም ፡ ይነጋል ብርሃን ፡ ተክቶ አይዘኝ ፡ ሃሳብ ፡ ትካዜ ይሆናል ፡ ሁሉ ፡ በጊዜ (፪x) አትጠጉት ፡ በቃ ፡ ድንጋይ ፡ አድርጉበት ፡ ሸትቷል ፡ መቃብሩ ጠብቀነው ፡ ነበር ፡ በጊዜ ፡ እንዲመጣ ፡ አክትሟል ፡ ነገሩ ሰው ፡ ደክሞት ፡ ሲጨርስ ፡ ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ይጀምራል በሞተ ፡ ነገር ፡ ላይ ፡ ይፈርዳል ፡ ሕይወት ፡ ይሰጠዋል ዝምታው ፡ ቢያስገርም ፡ የማያይ ፡ ቢመስልም አይቸኩል ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ ይፈርዳል ፡ በጊዜው ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው ሚነጋ ፡ አይመስልም ፡ ሌሊቱ ፡ ረዝሞ ጨለማውን ፡ አይቶ ሌሊቱም ፡ ያልፋል ፡ ደግሞም ፡ ይነጋል ብርሃን ፡ ተክቶ አይዘኝ ፡ ሃሳብ ፡ ትካዜ ይሆናል ፡ ሁሉ ፡ በጊዜ (፪x) ልቧ ፡ ያዘነባት ፡ ሁሌ ፡ ምታለቅሰው ፡ ልጅ ፡ የሌላት ፡ ሃና ታሾፍባት ፡ ነበር ፡ ነገ ፡ የሚሆነው ፡ ያልገባት ፡ ፍናና በጊዜው ፡ ፈረደ ፡ አምላኳ ፡ እንባዋን ፡ አበሰ ትውልድ ፡ የሚያወሳው ፡ ልጅ ፡ ሰጣት ፡ ሕይወቷ ፡ ተካሰ ዝምታው ፡ ቢያስገርም ፡ የማያይ ፡ ቢመስልም አይቸኩል ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ ይፈርዳል ፡ በጊዜው ታማኝ ፡ ነው ፡ ታማኝ ፡ ነው አንዳንዶች ፡ እንደዚህ ፡ ናቸው መከራው ፡ ሲበዛባቸው እምነታቸውን ፡ ሲጥሉ አይሰማም ፡ አያይም ፡ ሲሉ አለ ፡ ሁሉንም ፡ የሚያይ ከላይ ፡ ከሰማይ (፪x) ስለዚህ ፡ አትታበዩ በኩራት ፡ አትናገሩ እግዚአብሔር ፡ ሁሉን ፡ ያውቃል ይፈርዳል ፡ ይፈርዳል
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out