Lyrics

ፍቅረኛ ነበርን እኔና አለሚቱ ንዋይ በለጠባት ማረካት ውበቱ ልቤን ሰበረችው እንክትክት አድርጋ መሽቶ ሚቀር መስሏት ለኔም የማይነጋ ክድሀለችና በግልፅ ባደባባይ ነግርሀለችና እንደሆነች አባይ እንግዲህ እወቅበት በጊዜ ተሰብሰብ በዚህ አያበቃም የአለሚቱ ሰበብ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ ይመስገን ገንዘብ አመል ገላጩ ጓደኝነትሽ ቀረ በእንጭጩ እኔም ሄዳለው ድምፄን አጉልቼ ፍቅርን ይዤ ንዋይን ትቼ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ ብርቅ ያረኩት እኔ ባንቺ መከዳቱ አንቺ ምን ታደርጊ ካልገባኝ እውነቱ በማር ቢለወስ ቃል ቅቤ ቢያቀልጥ ምላስ ምን ያረጋል ብለሽ ሁለት ካጣ አንድ ራስ በማር ቢለወስ ቃል ቅቤ ቢያቀልጥ ምላስ ምን ያረጋል ብለሽ ሁለት ካጣ አንድ ራስ ለአንገት የሚቀል የለም እንደራስ ችዬ ኖራለው አልሻም ትራስ ስንደልቅ ነበር አብረን ከበሮ ኪሴ ተቀዶ ባላውቅሽ ኖሮ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ ሳላውቅ አመልሽን ሆንኩኝ መዛበቻ ውልሽ የአጭር ጊዜ ከሞላለት ብቻ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ ፍቺኝ አለም (ፍቺ ፍቺ) በቃኝ አለም (በቃኝ በቃኝ) ይቅር አለም (ይቅር ይቅር) ዞርበይ አለም (ዞርበይ ዞርበይ) (ፍቺ ፍቺ) (በቃኝ በቃኝ) (ይቅር ... ዞርበይ ዞርበይ) አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ አለሚቱ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out