Lyrics

ደስ ይላል ደስ ይላል ያሰብኩት ተሳክቷል ዝንፉም ተቃንቷል የጎደለው ሞልቷል ድፍርሱም ጠራ ህልሜም ተፈታ የተመኘኋት እጄ ገብታ ብርሃን ፈነጠቀች ገና ወጣች ጀምበር እስከዛሬ ለኔ ተደብቃኝ ነበር ከአደይ የደመቀች የቆንጆ መለኪያ የኩራቴ ምንጭ የዓይኔ መርኪያ በዕውቀት በጨዋነት ተሟልቷል ውበቷ እስክትገረም ሴቷ በሴቷ ከዓይን ያውጣሽ ነው እንጂ ሌላ ምን እላለሁ እኔን ስለመረጥሽ አመሰግናለሁ ኩራቴ ነው ሲያደንቁሽ አብሮ ይነሳል የእኔነትሽ ስሜ ነሽ ደስ ይላል ደስ ይላል ያሰብኩት ተሳክቷል ዝንፉም ተቃንቷል የጎደለው ሞልቷል ድፍርሱም ጠራ ህልሜም ተፈታ የተመኘኋት እጄ ገብታ ቀልዱን ቁምነገሩን አቤት ስታውቅበት ብትርቅ አይረሳት አትጠፋም ከአንደበት ስለጸባይዋማ አገር ምድሩ ያውቃል ብሽነፍላትም ምን ያስደንቃል ብቸኝነት በሷ ሲገለጥ ከላዬ ጸዳል ለበሰ ሁለመናዬ አሁን አማረብኝ ፍክት እለ መልኬ እንደ ፍላጎቴ ቢሰጠኝ አምላኬ እኖራለሁ ተደስቼ ሞገስ ክብሬን አንቺን አግኝቼ ምን አጥቼ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out