Similar Songs
Credits
PERFORMING ARTISTS
Nhatty Man
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Natnael Ayalew Yimer
Songwriter
Lyrics
አለኝ ጉዳይ አለኝ ጉዳይ
አለኝ ጉዳይ ሀገሬ ላይ
አለኝ ጉዳይ አለኝ ጉዳይ
አለኝ ጉዳይ
እግሩ እንደመራው በፊናው ወቶ
ባላሰበበት ቢቀርም ርቆ
ሁሉም ባለበት በቸር ያቆየው
ቀን እንደገፋው ቀን እስኪዳኘው
ዘሎ ቦርቆ በምድርሽ ላይ
የልጅ መልኩ ወዝቶ ባፈርሽ ሲሳይ
ማንስ ጨክኖ ፊቱን ባንቺ አዞረ
እንዴትስ ብሎ ሀገሩን ይጠላል
ያላለቀ ያልተቋጨ ሁሉ አለው ጉዳይ
ሀገሩ ላይ
ያላለቀ ያልተቋጨ ሁሉ አለው ጉዳይ
ኢትዮጵያ ላይ
ሸብ አርጎ
በፍቅር አስሮ
አንድ አርጎ
ሠብስቦ ልጆችሽን
ያለም ያርገው ደስታሽን
ሸብ አርጎ
በፍቅር አስሮ
አንድ አርጎ
ሠብስቦ ልጆችሽን
ያለም ያርገው ደስታሽን
ኑሮ ቢሞላ ወይም ቢጎድል
ለሀዘን ለደስታው ማን ያንቺን ያህል
ዘመን ግርማሽን ቢያደበዝዘው
ቤት አለኝ ማለት እሱም ኩራት ነው
ገመናሽ ቢወራ አልፎ ከማጀትሽ
አንገቴን አልደፋም ትልቅ ነው ታሪክሽ
ያላለቀ ያልተቋጨ ሁሉ አለው ጉዳይ
ሀገሩ ላይ
ያላለቀ ያልተቋጨ ሁሉ አለው ጉዳይ
ኢትዮጵያ ላይ
ሸብ አርጎ
በፍቅር አስሮ
አንድ አርጎ
ሠብስቦ ልጆችሽን
ያለም ያርገው ደስታሽን
ሸብ አርጎ
በፍቅር አስሮ
አንድ አርጎ
ሠብስቦ ልጆችሽን
ያለም ያርገው ደስታሽን
ያላለቀ ያልተቋጨ ሁሉ አለው ጉዳይ
ሀገሩ ላይ
ያላለቀ ያልተቋጨ ሁሉ አለው ጉዳይ
ኢትዮጵያ ላይ
ሸብ አርጎ
በፍቅር አስሮ
አንድ አርጎ
ሠብስቦ ልጆችሽን
ያለም ያርገው ደስታሽን
ሸብ አርጎ
በፍቅር አስሮ
አንድ አርጎ
ሠብስቦ ልጆችሽን
ያለም ያርገው ደስታሽን
ይሄ ነው ምኞቴ
ናፍቆት ፍላጎቴ
በህይወት እያለው
በዕድሜ በዘመኔ
እንዳየው ባይኔ
ይሄ ነው ምኞቴ
ናፍቆት ፍላጎቴ
በህይወት እያለው
በዕድሜ ዘመኔ
እንዳየው ባይኔ
Writer(s): Natnael Yimer
Lyrics powered by www.musixmatch.com