Lyrics

ንፋሱ ፡ ነፈሰና ፡ አለፈ ወጀቡም ፡ ጸጥ ፡ አለ ፡ አለፈ መንገዴን ፡ ዞር ፡ በዬ ፡ ሳየው ይህ ፡ ሁሉ ፡ ለመልካም ፡ የሆነው ስላለ ፡ ጌታ ፡ አጠገቤ ስላለ ፡ አባ ፡ አጠገቤ ከኖሩማ ፡ ኑሮ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ በችግር ፡ ቢሆን ፡ በመከራ ከተያዘም ፡ እጄ ፡ በአንተ ፡ እጅ ሕይወቴ ፡ ሰላም ፡ ነው ፡ የሚመች ስሄድ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ በሕይወት ፡ መንገድ ምንም ፡ ነገር ፡ አይሆን ፡ ያለ ፡ አንተ ፡ ፈቃድ አያስጨንቀኝም ፡ ነገ ፡ የሚሆነው የነፍሴ ፡ ፍጻሜ ፡ በእጅህ ፡ ነው የእኔ ፡ ነገር ፡ ሰው ፡ ይማይዘጋው ፡ ሰው ፡ የማይከፍተው ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው የእኔ ፡ ነገር ፡ መጀመሪያዬ ፡ መጨረሻዬ በእርሱ ፡ አይደል ፡ ወይ ከኖሩማ ፡ ኑሮ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ በችግር ፡ ቢሆን ፡ በመከራ ከተያዘም ፡ እጄ ፡ በአንተ ፡ እጅ ሕይወቴ ፡ ሰላም ፡ ነው ፡ የሚመች ሲጸልይ ፡ ዳናኤል ፡ አንተን ፡ ስለጠራ ጉድ ፡ ጓድ ፡ ውስጥ ፡ ከተቱት ፡ በአንበሳ ፡ እንዲበላ ይንከባከቡታል ፡ እንኳን ፡ ሊበሉት ችግር ፡ ይቀየራል ፡ በምቾት የእኔ ፡ ነገር ፡ ሰው ፡ ይማይዘጋው ፡ ሰው ፡ የማይከፍተው ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው የእኔ ፡ ነገር ፡ መጀመሪያዬ ፡ መጨረሻዬ በእርሱ ፡ አይደል ፡ ወይ ቆይ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ከአንተ ፡ የራቀ ፡ የተሰወረብህ እኮ ፡ ምን ፡ አለ ፡ አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ሁሉን ፡ የምታውቅ ቆይ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ድንገት ፡ ተገልጦ ፡ የሚያስደነግጥህ እኮ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ሰማይ ፡ ምድሩን ፡ ሁሉን ፡ በእጅህ ፡ ይዘህ መላ ፡ ሕይወቴ ፡ አምላኬ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ እድሜ ፡ ዘመኔ ፡ አምላኬ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ነገዬም ፡ ቢሆን ፡ አምላኬ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ እስትንፋሴ ፡ እንኳን ፡ አምላኬ ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out