Lyrics

ብዬሽ ዓለሜ እያለሽ ከእኔ ለካስ ሁለት ፊት ነሽ የሰዉ ቅኔ የማየው የዋህ እርግብ መልክሽን ፍቅር ጋርዶብኝ መብረርሽን አዬ-ዬ ብላቴናው ኖረ ሲታገስ አዬ-ዬ ሰምና ወርቅ እስኪለይ ድረስ አዬ-ዬ ይብላኝ ለዘረፈሽ ከኔ አዬ-ዬ የፈታሁሽ የሰው ቅኔ (ተው ምነው ክራሬ ተው ምነው) (ከድታ የሄደችን ታመጣለህ ምነው) ጀምረን ነበረ ፍቅርን እንድ ድውር የጥጥ ቃላት ክምር በቀናቶች ዝውር ጥለቱን በመልኳ አሳምሬ ነድፌው "ቋጪው" ብላት "እንቢ" ብቻዬን ጠልፌው ዓባይን ብከተል ሰጠኝ ለፈርዖን መጨረሻው ሀዘን ያንቺ አፍቃሪ መሆን እራሴን ከልቤ አጣልተሽብኝ ሰው አልሆንም ነበር እርሱ ባያየኝ አዬ-ዬ ብላቴናው ኖረ ሲታገስ አዬ-ዬ ሰምና ወርቅ እስኪለይ ድረስ አዬ-ዬ ይብላኝ ለዘረፈሽ ከኔ አዬ-ዬ ፈታሁሽ የሰው ቅኔ ጀምረን ነበረ ፍቅርን ማሾር እንደድውር ፈትለን ነበር ቀጭን ፍቅር በቃላቶች ዝውር ጥለቱን ልክ እንደመልኳ አሳምሬ ነድፌው "ቋጪው ብላት "እንቢ" ብቻዬን ጠልፌው አይ ብታዩ ማማሩን ድንቁን ስራዬን?! ከኔ የዘረፈሽ መቼም የማይሰጥሽን ብቻዬን ጠልፌ ላንቺ የሰራውትን ሸማ ላደላት አስቀመጥኩላት ካልቋጨሽውማ ሀ ግዕዝ ሁ ካልዕ ብሎ ሂ ሳልስን አስከትሎ አስከትሎን አስከትሎ የጀመረው በአቦጊዳ ለፍቅር ነበር እንግዳ፤ አይ እንግዳን አይ እንግዳ ብላቴናው ኖሮ ሲታገስ ቅኔ እስኪገባው ድረስ፤ ድረስ ድረስ ወርቁን ያገኝሁለት ያኔ ፈታሁሻ የሰው ቅኔ (የሰው ቅኔ፣ የሰው ቅኔ፣ የሰው ቅኔ) (ህ-ህ-ምም) ትዝታየን ትቼ ቅኝት ሌላ ይህወት ሀ ሁ እንደገና ትዝታየን ትቼ ቅኝት ሌላ እያየሁሽ ወደ ኋላ ትዝታየን ትቼ ቅኝት ሌላ ይህወት ሀ ሁ እንደገና ትዝታየን ትቼ ቅኝት ሌላ ግን ፊት የለም ግድ ነውና (ህ-ህ-ምም) (ህ-ህ-ምም) (ህ-ህ-ምም) (ህ-ህ-ምም) (ህ-ህ-ምም) (ህ-ህ-ምም) (ህ-ህ-ም-ምምም ህ-ም-ም-ምምም) (ዬ-ህ)
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out