Lyrics

የኔማ ልጅ ሚካኤል ልጅ ሚካኤል ብላለች እናቱ ስም አዉቃ የረከሰ አይነካም እንደ ታቦት እቃ የኔማ ልጅ ሚካኤል አንተን የወለደች ባየዋት እናትህን የተሞላ ቢራ አስመስላ አንገትክን የእንግሊዝ ብረጭቆ አስመስላ አንገትክን የኔማ ልጅ ሚካኤል እኔስ ለገንዘብህ ስም አታረግብኝ በሄድክበት ቦታ ደና ሁንልኝ የኔ አድለ መልካም የኔ ስመ መልካም በእግሩ ፍሬን እንጂ በአፉ ሰዉ አይነካም የኔማ ልጅ ሚካኤል ሰማይ ልኩ ኮከብ ሰማይ ልኩ ኮከብ አጥማቂዉ ጨረቃ ቅዱስ ሚካኤል ነዉ ያንተ ዋስ ጠበቃ መላዕኩ ገብርኤል ነዉ ያንተ ዋስ ጠበቃ እስከመጣሁባት ምድር ሰዉን ከማስደሰት በቀር አይወጣኝም ክፉ ነገር የጥሩ ሰዉ ዜማ ከላይ ተሰቀለ መኖር ነበረባት ብዙነሽ በቀለ የኩባያ ወተት የለዉም አረፋ በሽታዬን የሚያቅ አስታማሚ ጠፋ ጥሩ ሰዉ ከለየ በዳሰሳ መልኩ ተሾመ አሰግድ የጥበብ ሰዉ ልኩ ከዚ በላይ ጥበብ ከየት ይመጣል ልኩ ልበ ብርሃን ሲባል ትርጉሙ ካልገባሽ ዉረጅ ተመለሺ ቢሉሽም የት ነበርሽ የት ነበርሽ ቢሳካ መንገዴ ዳር እና መሀሉ ሲገምቱኝ ዉለዉ በስም እየማሉ ሚስጥረኛ መፅሀፍ አንብቦ ነዉ አሉ ገረመኝ ስሰማ መወራረዳቸዉ ሚተካዉ አይጠፋም እሱን ማለታቸዉ አዬ ተወራረድ ተብሎ ቢሰጠኝ እድል ባለኝም በሌለኝ ብያዝም ወገቤ እወራረዳለዉ ደግሜ ደግሜ ባህሩ ቃኜንስ አይተኩትም ብዬ አባ ወዴ ሰማው ቆመዋል ወይ ከበሬ ሊሞገስ ነዉ መሰል ዉሎና አዳሬ እሽት እሽት አርገዉ ጤናዳም በሻይ ጨብጠዉ ሚሄደዉ በረካ ነዉ ወይ ገበታ በመሶብ ሳይዘጋ በር ልማድሽ ነበረ ከጎረቤት ጋር ከራስሽ የዉጣ ስምሽን የማይጠራ ከገበታዉ ዘሩን ጀመረ ቆጠራ እኔ አላዉቅልሽም አልልም እርግማን ብቻ አደራሽን ደግመሽ እንዳትወልጅው ከዘርም ዘር አለ የሚበላ እንደገብስ ሰዉ እንዴት በዘሩ ይበላል የሰዉ ነፍስ ይታረሳል መሬት ኧረ በላይ በላይ ከዛ እስከዚ ድረስ መጣዉ በሬሳ ላይ ወዴት ሄደ በሬዉ የቦታዉ አለቃ አጋቹስ ምን ሆነ ተኝቶ ማይነቃ ጠጥቶ ነዉ አሉኝ ያንን ካቲካላ እኛ አናቅም አሉ ዳሂራ እንደጠጣ ሰዉ ሀገር ወዳድ አይደል ልበ ገራገሩ ያልበጁለት ሴራ ከበር እስከ በሩ ለዉሰዉ ቢሰጡት ክፋትን በማሩ ከክፋቱ በላይ አረ ጎላ ማሩ እስከመጣሁባት ምድር ሰዉን ከማስደሰት በቀር አይወጣኝም ክፉ ነገር የጥሩ ሰዉ ዜማ ከላይ ተሰቀለ ብትኖር ጥሩ ነበር ብዙዬ በቀለ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out