Lyrics

በዘመድ ተከባ በሰፈር ግዛት ሁሉም ይፈራታል የሴት አንበሲት እኔም በአንቺ ስም ታማው በሰፈሩ ስሜ ካንቺ በፊት ነበረ ደፋሩ ማማዬ ማማዬ ቆንጆ ልጅ ማማዬ ማማዬ ማማዬ ማማዬ ማማዬ ቆንጆ ልጅ ማማዬ ማማዬ ማማዬ ገዳም ዋለች አሉ ሄዳ አደረች እዛ ማማዬ ማማዬ ኧረ እንዴት ቻለችው የሰውን ልብ ይዛ ማማዬ ማማዬ የማማርን ትርጉም የጸዳልን ፍቺ በማን ላስነግረው ካልሆነማ ባንቺ ሄደች አቀናችው ልከተላት እኔ እሷም በቁንጅና ወንድም ልጅ በወኔ እቴ ተነሽ ተነሽ አምረሽ በሽመና ለመሬቱም አንቺ ሌላኛው ደመና እዳለሽ ቆይለት ያማርሽበት ድረስ የቀባሽን ቅባት እስክናውቅው ድረስ እቴ ምንሽን ነው ቀኑን የሚያሙሽ አማረባት ይሆን ካፍ የከተተሽ እኔ እረፊ ብዬ ተናግሬ ነበር እንዲ ያማረባትን ቀርቦ ማነጋገር ሰው አቅም አነሰው ቀኑ እየተናጋ ስላንቺ ሲናገር ሳይመሽ እየነጋ ማማዬ ማማዬ ቆንጆ ልጅ ማማዬ ማማዬ ማማዬ ማማዬ ማማዬ ቆንጆ ልጅ ማማዬ ማማዬ ማማዬ ገዳም ዋለች አሉ ሄዳ አደረች እዛ ማማዬ ማማዬ አረ እንዴት ቻለችው የሰውን ልብ ይዛ ማማዬ ማማዬ ድርብብ ያለች ደርባባ የምታምር አበባ የከተማ ወለባ የተሰራች ሹሩባ የትልቅ ልጅ ክብርቷ እቴ የሚሏት በቤቷ በቤቷ በቤቷ እንደ ልቤ እንደ ስሜቴ ለኔስ ያለኝ ባቅም ባንገቴ የተስማማች ለኔስ አንደኛ ሁሏ ፍቅር የሆነ ማኛ ዘመዳ ዘመዱ የኔ የምላቸው እንዴት ነህ ይሉኛል እንዴት ልበላቸው አመል ከቁንጅና ለጉድ ተሰጠና ወንድ ልጅ በከባድ ገጠመው ፈተና ኧረረረ ያለው ያገር ጀግና ለካ ተወግቶ ነው ልቡን በቁንጅና በታችም በላይም ዝናው ሊመታ ነው ልቤም እሷን ይዞ በዋስ ሊፈታ ነው ዘመዳ ዘመዱ የኔ የምላቸው እንዴት ነህ ይሉኛል እንዴት ልበላቸው ማማዬ ማማዬ ቆንጆ ልጅ ማማዬ ማማዬ ማማዬ ማማዬ ማማዬ ቆንጆ ልጅ ማማዬ ማማዬ ማማዬ ገዳም ዋለች አሉ ሄዳ አደረች እዛ ማማዬ ማማዬ አረ እንዴት ቻለችው የሰውን ልብ ይዛ ማማዬ ማማዬ
Writer(s): Samuel Alemu, Michael Taye Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out