Lyrics

Yeah yeah (Yoni on the beat) ተወዉ በከተማዉ ጭራሽ በሰፈሩ አንተን የሚመስል አለ ወይ በሀገሩ ተይዉ በከተማዉ ጭራሽ በሰፈሩ አንቺን የሚመስል አለ ወይ በሀገሩ ከዛ እስከዚህ ድረስ መጣዉ አንተን ብዬ የፍቅር መድኃኒት ብትሆነኝ ብዬ ያገር የከተማዉ የሰፈሩ ራፐር ልጅ ሚካኤል መጣ ቀንሽ ይስተካከል ትዉልዴ አዲስ አበባ የገባኝ አራዳ በፍቅር ጨዋታ ማንም እንዳይጎዳ ፍቅርን በሂፕ ሆፕ እንደዚ ሳወርደዉ ፍቅርን በሂፕ ሆፕ እንዲ ስዘክረው ፈታ በይ ያገር ልጅ ጭንቀቱ ምንድነዉ ደሞስ ከኛ በላይ ማን አለ ተብሎ ነዉ ሁሉም ይመኝሻል ይወድሻል ያይሻል የት ቢሄዱ የት ቢመጡ ያገኙሻል ተነሺ ተጫወች የምን ጉድ ጉድ ዛሬ እረፍት ነዉ ልክም እንደ እሑድ ለፍቅር ጨዋታ ቢዘጋም መንገድ አይዞሽ የገባዉ ነዉ የሂፕ ሆፕ ነገድ ተወዉ በከተማዉ ጭራሽ በሰፈሩ አንተን የሚመስል አለ ወይ በሀገሩ ተይዉ በከተማዉ ጭራሽ በሰፈሩ አንቺን የሚመስል አለ ወይ በሀገሩ ከዛ እስከዚህ ድረስ መጣዉ አንተን ብዬ የፍቅር መድኃኒት ብትሆነኝ ብዬ አንቺ መልከ ቀና ገራሚ የቤት ልጅ እኔ ደሞ ራፐር ያዉም የሰፈር ልጅ ፍቅር አያዉቅልሽ ብለዉ ቢነግሩሽ ይዘቱ ቢለይም እኔዉ ላሳይሽ ጠጋ በይ ወደእኔ አትፍሪ ግቢበት እንደኛ ነበሩ ንግሥተ ነገሥታት ሳቅ እና ጨዋታሽ የሕመም መድኃኒት ስንቴ ከሞት አፋፍ የተነሳሁበት ሁሉም ይመኝሻል ይወድሻል ያይሻል የት ቢሄዱ የት ቢመጡ ያገኙሻል ከሌለሽ ይዝታል ቤቱ ሲሆን ባዶ ወንድ ልጅ ተያዘ ክፉኛ አንቺን ለምዶ ደስታ እና ፈገግታ ከፊትሽ ለምጄ ወዴት ልንቀሳቅስ ወዴት ልምጣ ሄጄ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out