Lyrics

አብዱ ኪያር - ABD የላይ ላዩን ብቻ እያያችሁ የላይ ላዩን ብቻ እያያችሁ ተመችቶታል አትበሉ የኔ ነገር መቼ ገባችሁ ያጣሁትን ማን አወቀልኝ ጉዳቴንስ ማን ተረድቶታል ፍቅር ፍቅር ይላል ገላዬ ብቸኝነት አስጠልቶታል በልቼ ጠጥቼ ኖርኩኝ ሊባል ነው ወይ አለመፌቀሬ ውርደት አይደለም ወይ ፍቅር የለሽ ኑሮ ኑሮ ከተባለ ኤ ቢ ዲ ከእንስሳ በምኑ ተሻለ ለኔ ያለልኝን ለኔ ያለልኝን እድሌን ልጠብቅ እሱ የመረጠልኝን በልቼ ጠጥቼ ኖርኩኝ ሊባል ነው ወይ አለመፌቀሬ ውርደት አይደለም ወይ ፍቅር የለሽ ኑሮ ኑሮ ከተባለ ኤ ቢ ዲ ከእንስሳ በምኑ ተሻለ ባዶ ቤቴ ያባዶ ቤቴ ሙሉ መስሎ የሚታያችሁ ፍቅርና ደስታን እንዳጣ አፍ በኖረው በነገራቸሁ ያለ ፍቅር ያለ ፍቅረኛ ለብቻዬ እየኖርኩበት ተመችቶታል አትበሉኝ የኔ ኑሮ መከራ አለበት በልቼ ጠጥቼ ኖርኩኝ ሊባል ነው ወይ አለመፌቀሬ ውርደት አይደለም ወይ ፍቅር የለሽ ኑሮ ኑሮ ከተባለ ኤ ቢ ዲ ከእንስሳ በምኑ ተሻለ
Writer(s): Abdu Kahssay Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out