Lyrics

ቀራንዮ ቀራንዮ ጐለጐታ ባንቺ ምድር ያለም ጌታ ተጨነቀ ተሰቃየ ተንገላታ በማይቀለ ምድር ዙፋን መስቀል ተክሎ ልብስን አለበሰን እርቃኑን ተሰቅሎ ስራችን ተሻረ በመከራ ቆስሎ ቁስላችን ተሻረ በመከራ ቆስሎ ያማረ ልብስ የለው ደም ሆኗል ቀሚሱ የወርቅ ካባ የለው እርቃኑን ነው እሱ በፍቅር ይገዛል ተሰቅሎ ንጉሱ ቀራንዮ ቀራንዮ ጐለጐታ ባንቺ ምድር ያለም ጌታ ተጨነቀ ተሰቃየ ተንገላታ የስልጣኑ በትር በእጁ የያዘው ሳዶር እና ናዶር የበትር ሚስማር ነው እየቸነከሩት አላማው ፍቅር ነው ሞታችንን ወስዶ ሂወቱን ሸለመ ህሙማንን ሊያድን ለፍቅር ታመመ ከውድቀት ሊያነሳን ወደቀ ደከመ ቀራንዮ ቀራንዮ ጐለጐታ ባንቺ ምድር ያለም ጌታ ተጨነቀ ተሰቃየ ተንገላታ ስለኛ ብለህ ተንገላታህ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out