Lyrics

እንደምህረትህ ብዛት ማረኝ መተላለፌን ደምስስልኝ አንተን ብቻ በደልኩኝ ትእዛዝህን ተላለፍኩኝ አንተን ብቻ በደልኩኝ ትእዛዝህን ተላለፍኩኝ እጅግ በዛ የኔ ኃጢያት ከፀጉሬ በመቅደስህ እጮሃለው አቀርቅሬ አትቅሰፈኝ በመዓትህ አትግስፀኝ ጌታዬ ሆይ የማዳንን ደስታን ስጠኝ አትቅሰፈኝ በመዓትህ አትግስፀኝ ጌታዬ ሆይ የማዳንን ደስታን ስጠኝ እንደምህረትህ ብዛት ማረኝ መተላለፌን ደምስስልኝ አንተን ብቻ በደልኩኝ ትእዛዝህን ተላለፍኩኝ አንተን ብቻ በደልኩኝ ትእዛዝህን ተላለፍኩኝ እንደማወቅህ ባደባባይ ምን ብናገር ስራዬ ግን ይሄን እውነት አይመሰክር ከእልፍኝህ ብሄድ ርቄ ካንተ ፍቅር ሁሉን ከሰርኩ አላተረፍኩ አንዳች ነገር ከእልፍኝህ ብሄድ ርቄ ካንተ ፍቅር ሁሉን ከሰርኩ አላተረፍኩ አንዳች ነገር እንደምህረትህ ብዛት ማረኝ መተላለፌን ደምስስልኝ አንተን ብቻ በደልኩኝ ትእዛዝህን ተላለፍኩኝ አንተን ብቻ በደልኩኝ ትእዛዝህን ተላለፍኩኝ ማን እንደ እኔ ከትውልዱ የበደለ መኃሪ አምላክ ካንተ በቀር ወዴት አለ የዳዊት ልጅ ማረኝ ብዬ እጮሃለው እያነብሁ በጉልበቴ እሰግዳለው የዳዊት ልጅ ማረኝ ብዬ እጮሃለው እያነብሁ በጉልበቴ እሰግዳለው እንደምህረትህ ብዛት ማረኝ መተላለፌን ደምስስልኝ አንተን ብቻ በደልኩኝ ትእዛዝህን ተላለፍኩኝ አንተን ብቻ በደልኩኝ ትእዛዝህን ተላለፍኩኝ በመዳፈር እንደ አፍኒን እንደ ፊናሐስ ሰውነቴን አቆሸሽኩኝ ያንተን መቅደስ አሳልፈህ እንዳትሰጠኝ ለኃጢያቴ እንደ ቀድሞ ልጄ በለኝ ደጉ አባቴ አሳልፈህ እንዳትሰጠኝ ለኃጢያቴ እንደ ቀድሞ ልጄ በለኝ ደጉ አባቴ እንደምህረትህ ብዛት ማረኝ መተላለፌን ደምስስልኝ አንተን ብቻ በደልኩኝ ትእዛዝህን አፈረስኩኝ አንተን ብቻ በደልኩኝ ትእዛዝህን አፈረስኩኝ
Writer(s): Samuel Alemu, Abel Mekbib Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out