Lyrics

በእንባዬ የማመልክህ ጌታዬ ከክፉ ቀን መውጫ አንባዬ ሃዘኔን በደስታ ለውጠው አንተን በመታመን ልለፈው አንተን በመታመን ልለፈው ከእናቴ ማህፀን እያለሁኝ ገና የተደገፍኩብህ አምላኬ ነህና አውጣኝ ከመከራ እያልኩኝ ቀን ለሊት ምንጣፌን ዘወትር በእንባዬ አራስኩት ምንጣፌን ዘወትር በእንባዬ አራስኩት በእንባዬ የማመልክህ ጌታዬ ከክፉ ቀን መውጫ አንባዬ ሃዘኔን በደስታ ለውጠው አንተን በመታመን ልለፈው አንተን በመታመን ልለፈው የምትታመነው ሁልጊዜ ምትጠራው እያሉ ሲወቅሱኝ አምላክህ ወዴት ነው ለአፌ ምግብ ሆነኝ የማነባው እንባ እባክህ አምላኬ ወደእረፍቴ ልግባ እባክህ አምላኬ ወደእረፍቴ ልግባ በእንባዬ የማመልክህ ጌታዬ ከክፉ ቀን መውጫ አንባዬ ሃዘኔን በደስታ ለውጠው አንተን በመታመን ልለፈው አንተን በመታመን ልለፈው እስክትጎበኘኝ ከሰማዩ መቅደስ ማዳንህን እስካይ እንባዬ እስኪታበስ ሳታቋርጥ እንባን ታፈሳለች አይኔ እንደ ቀድሞ ይሁን ይታደስ ዘመኔ እንደ ቀድሞ ይሁን ይታደስ ዘመኔ በእንባዬ የማመልክህ ጌታዬ ከክፉ ቀን መውጫ አንባዬ ሃዘኔን በደስታ ለውጠው አንተን በመታመን ልለፈው አንተን በመታመን ልለፈው ከአንደበቴ ጠፍቷል የፅዮን ዝማሬ በባቢሎን ምርኩዝ አለው አቀርቅሬ በዛ የማረኩን ፈለጉ እንድዘምር እንዴት ይቻለናል በባዕዳን ምድር እንዴት ይቻለናል በባዕዳን ምድር በእንባዬ የማመልክህ ጌታዬ ከክፉ ቀን መውጫ አንባዬ ሃዘኔን በደስታ ለውጠው አንተን በመታመን ልለፈው አንተን በመታመን ልለፈው
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out