Lyrics

ደህና ሰንብት ብዬ ውለታዬን ልሸኘው አብሮ መብላትንም አየሁት ስመኘው እንግዲህስ ጥሎኛል ሰው ማመን ዳግመኛም እንዳልቃኘው ደህና ሁን እያልኩኝ ማመንን ልሸኘው ሀዘን ያልፋል ብዬስ መልሼ አልቃኘው አልሆንልህ ብሎኛል ሰው ማግኘት ብጓጓለት ብመኘው ቻልልኝ እያልኩት አንጀቴን ከመጨነቅ ላውጣው ለሰው መራራት ነው እያደር ቅርሱን የሚያሳጣው ያስጠቃው ያስቀጣው እንግዲህስ እጄን አንስቼ ምን ልቋደስበት ሲያገኝ ለሰው ለሰው እያለኝ እያጎረስኩበት ከተነከስኩበት ይቅር የኔስ ማመን አለበጀም አልቆየም ከቦታው ለሰው የደገስኩት ደግነት ዋንጫና ገበታው ተሰብሯል እውነታው አንጀቴን አየሁት ሆዴንም ታዘብኩት የከዳን ለመርሳት ይችላል እያልኩት አይጨክን ያለ ሰው አይበላ አንጀቴ እየላላ ቢበቃኝ ባዝል ያልጠበቅኩትን ይደርሳል ያሰብኩት ደህና ሰንብት ብዬ ውለታዬን ልሸኘው አብሮ መብላትንም አየሁት ስመኘው እንግዲህስ ጥሎኛል ሰው ማመን ዳግመኛም እንዳልቃኘው ደህና ሁን እያልኩኝ ማመንን ልሸኘው ሀዘን ያልፋል ብዬስ መልሼ አልቃኘው አልሆንልህ ብሎኛል ሰው ማግኘት ብጓጓለት ብመኘው ወዳጅነትንም አየሁት ካ'ንዴም ሁለት ሶስቴ ከሰው ጋራ ልኖር እያልኩኝ እጄን በመክፈቴ ፈርሶብኛል ቤቴ አብሮ መብላት ቢበጅስ እኔን መች ረዳኝ ችዬ አይቼ ተውኩት እያደር ያመንኩት ሲከዳኝ ደግነት ሲጎዳኝ ይብቃኝ የሰው ነገር ከእንግዲህ ጥቃቱ እስጨከነኝ ተበድዬም ስችል ይሁን ስል ደግሞ እያሳዘነኝ ሰው ማመን ተሳነኝ አንገቴን ሰበርኩት አይኔንም ሸፈንኩት ከእንግዲህ ሰው ማየት ይበቃል እያልኩት ቢመስለኝ ብጫወት ብስቅም ሰው ሆኖኝ አያውቅም ምን ቢያምር ፍቅሩ እስኪጠነሰስ አይቀር ከመደርመስ ሲደገስ ሲወጠን ቢደምቅም ተጀምሮ አያልቅም ሲጀመር ሲደገስ ቢደምቅም እንደአማረ አይዘልቅም ሲጀመር ሲደገስ ቢደምቅም ተጀምሮ አያልቅም
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out