Lyrics

የጎኔ ባላ ማገር ስላንቺስ ምን ልናገር አይጎልም አያልቅም እንጀራሽም ሲጋገር የጎኔ ባላ ማገር ስላንቺስ ምን ልናገር አይቀልም አይሳሳም እንጎቻሽም ሲጋገር ከደሜ የተገኘሽው ትርፌ ግምቴ ያኮራል ይሞቃል ባንቺ ይደምቃል ቤቴ አልጥልሽም አልንቅሽም ካፈራሽ ጉልበቴ ከራቀ ከቀለለልኝ ስጋት ትካዜ ካለልኝ ከቀናኝ ኑሮ ባንቺው ማዘዜ ያዝልቅልኝ ያክርምልኝ ልደሰት በወዜ ምኞቴን ከመጠንኩት እንደራስ ካደረግኩት ከበቃሁስ ለጉርሴ እንዳቅም እንደኪሴ አይቀርም እንደሰው አንጀቴን ማራሴ አንጀቴን ማራሴ ከሰው ፊት ከረመጡ ከማለቅ ከመቅበጡ ሰው ልብን ከታደለ እራስን መቻል ካለ ኑሮም መከታው ነው ከተስተካከለ ከተስተካከለ የጎኔ ባላ ማገር ስላንቺስ ምን ልናገር አይጎልም አያልቅም እንጀራሽም ሲጋገር የጎኔ ባላ ማገር ስላንቺስ ምን ልናገር አይቀልም አይሳሳም እንጎቻሽም ሲጋገር ሰው ነጥቆም ከስንፈት ወድቆ ካልከፋ ስሙ እምሽክሽክ ብሎም ካልቀረ ተሰብሮ ቅስሙ እጁ አይነጥፍም ክንዱ አይመክንም ከለፋስ እንዳቅሙ ከደስታው ከኑሮውም ኑሮው የጎደለበት የከፋው አግኝቶም ማጣት ያንዣበበት ያገግማል ወረቱ አልቆ ቀን የጨለመበት ለተራው ለፈረቃው ቢከታተል ሰቆቃው ሰው ቅስሙን ሳይባበር ስራን ቢያይ እንደክብር በምድር ያፈራው ስም አይገባም መቃብር አይገባም መቃብር በወዙም እያደረ ቅሪቱን ከቋጠረ አዙሮም ካስተዋለ መከራን ያልፋል ካለ ቢቀጥንም አንገት ነው እራስን ከቻለ እራስን ከቻለ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out