Lyrics

አለም ሸጋዬ ሆይ እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ አንቺ ሸጋ ጉብል እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ አለም ሸጋዬ ሆይ እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ ይቺ የወሎ ልጅ አንገተ ዥጉርጉር ይቺ የአምባሰል ልጅ አንገተ ዥጉርጉር መንገዱን አስላ ሰደደችኝ በዱር መንገዱን አስላ ሰዳኛለች በዱር ወሎ መሄዴ ነው እኔስ ለሽርሽር ከቆንጆዎች ጋራ እያልኩኝ ያዝ አብሽር ኧረ ዘመድዬ ኧረ ዘመድዬ ኧረ ዘመድዬ እንጃ እንጃ አንቺዬ ከመከም አለችኝ እንደምን ልከምከም ሀኪሜም እሷው ናት አምጡልኝ ልታከም እስክስታ አወራረድ አይችልም ጉልበቴ እንደው መታ መታ መላው ሰውነቴ ነይ ሰውነቴ ነይ ነይ ነይ ሰውነቴ ነይ ነይ አለም ሸጋዬ ሆይ እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ አንቺ ሸጋ ጉብል እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ አለም ሸጋዬ ሆይ እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ የባህል ቀሚሱን ድሪውን አርገሻል ፀጉርሽን ሹርባ አሰርተውሻል አንገትሽን በሾህ አስነቅሰውታል ጣትሽን በእንሶስላ አሳምረውታል ይህ ሁሉ መኳኳል ምን ያደርግልሻል ወሎዬ ነኝ ብትይ ስሙ ይበቃሻል ኧረ ዘመድዬ ኧረ ዘመድዬ ኧረ ዘመድዬ እንጃ እንጃ አንቺዬ ከመከም አለችኝ እንደምን ልከምከም ሀኪሜም እሷው ናት አምጡልኝ ልታከም እስክስታ አወራረድ አይችልም ጉልበቴ እንደው መታ መታ መላው ሰውነቴ ነይ ሰውነቴ ነይ ነይ ነይ ሰውነቴ ነይ ነይ እጥፍ ዘርጋ እያለች የልቤን ሰላይ መጣች የወሎ ልጅ በገራዶ ላይ በወልድያ በኩል እያለች ዘው ዘው መጣች አንዱን ልቤን ልትወሰውሰው በአምባሰል ዙረሽ በእመቤቴ ማርያም ለነፍሴ ድረሽ ኧረ ዘመድዬ ኧረ ዘመድዬ ኧረ ዘመድዬ እንጃ እንጃ አንቺዬ ከመከም አለችኝ እንደምን ልከምከም ሀኪሜም እሷው ናት አምጡልኝ ልታከም እስክስታ አወራረድ አይችልም ጉልበቴ እንደው መታ መታ መላው ሰውነቴ ነይ ሰውነቴ ነይ ነይ ነይ ሰውነቴ ነይ ነይ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out