Lyrics

ቀን ሲያልፍ አመረረች በቃ አትመጣም አልቆባታል የፍቅሬ ጣዕም ከእንግዲ እኔም ልተው ከተወቺኝ ፍቅሬን ትታ ከረሳችኝ በአደባባይ ቆሜ ስለምናት ማሰብ ከብዶኝ እሷን ማጣት ጭላንጭል ተስፋ እንኳ በሷ ጉዳይ የሚያሳየኝ በር ባላይ ቻው "ቻው ቻው" ትልና ተሰናብታኝ ሄዳ ደሞ ትመጣለች ያለ'ኔ አልችል ብላ ቻው "ቻው ቻው" ትልና በቃህኝ በቃህኝ ደሞ ትመጣለች አይንህ ላፈር ብላኝ እረ ጉድ ናት! ዞሬ ከእግሯ ስር ስር ከደጇፏ አይደለችም ልክ እንዳፏ ስትመጣ ተቀባይ ሸኚ ስትሄድ ሆኗል ልቤ አሽከር መንገድ ምን እንደሚያለያየን አላውቅም ስትመጣም አልጠይቃትም መውደድ አስሮ ገዝቶ ለጉሞኛል እንደ ግዑዝ አስቀምጦኛል ቻው "ቻው ቻው" ትልና ተሰናብታኝ ሄዳ ደሞ ትመጣለች ያለ'ኔ አልችል ብላ ቻው "ቻው ቻው" ትልና በቃህኝ በቃህኝ ደሞ ትመጣለች አይንህ ላፈር ብላኝ እረ ጉድ ናት! ልቤን በ'ጁ ፍቅር እየዘወረው ትንፋሽ ውስጤን እያጠረው እኔ እያልኩ ለሰዎች አሸማግሉኝ እሷ እያለች ውይ ገላግሉኝ ከዚ ኃላ ብዬ ተገዝቼ ስትርቅ ካ'ይኔ ስንት ዝቼ ገብቷት ማጠፊያ መዘርጊያው ልቤ አልውል በሷ እንዳሳቤ አሄሄ አሃሃ አሄሄ አሃአሃአሃ ጎራ እያለች ስዘጋጅ እንዳለምድ ሌላ ወዳጅ ሃሳቤን ስትሄድ አስታኝ ወይ ትታ አተወኝ እረስታኝ ዳኙኝ አዋዩኝ 'ባካችሁ የምታውቁ አፍቅራችሁ እሷ ብልጥ የቆቅ ዘመድ እኔ ያለኝ አንድ መውደድ ቻል ቻል ቻል አድርጌው እንጂ ባጣ ሰው አስረጂ ቻው ቻው ብሎ የሄደ ሰው መመለሱ ምነው? ቻው "ቻው ቻው" ትልና ተሰናብታኝ ሄዳ ደሞ ትመጣለች ያለ'ኔ አልችል ብላ ቻው "ቻው ቻው" ትልና በቃህኝ በቃህኝ ደሞ ትመጣለች አይንህ ላፈር ብላኝ እረ ጉድ ናት!
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out