Lyrics

ምን ትጠብቃለህ (አቦ ሸማኔ አቦ) አንዲያ ወዲያ ወዲህ (አቦ ሸማኔ አቦ) ትንቆራጠጣለህ (አቦ ሸማኔ አቦ) በሰፋው ደረትህ (አቦ ሸማኔ አቦ) ባማረው ባትህ (አቦ ሸማኔ አቦ) እስኪ ተለመነኝ (አቦ ሸማኔ አቦ) በአይንህ በጥርስህ (አቦ ሸማኔ አቦ) የሰው ስጋ እርም ነው (አቦ ሸማኔ አቦ) ይቅር መብላትህ (አቦ ሸማኔ አቦ) ሸማኔ አደራ ብሰጠው አደራ ልቤን በልቶት ተገኘ አሉ በጣጥሶ አንጀቴን የደከመን ገሎ ፉከራ ምንድነው ቀን የጣለው ለታ እሱም የኔ ነው እርም የናቴን ስጋ እምልልሃለሁ ፍቅርን ካልሰጠኸኝ እሞትብሃለሁ ያን እንቢ ያን እንቢ ስለመን ከርሜ ይሄው ተጃጃልኩኝ ደግሜ ደግሜ ደግሜ ደግሜ ደግሜ ደግሜ ደግሜ ደግሜ ደግሜ ባቱ ተረከዙ (አቦ ሸማኔ አቦ) ስጋው ተነባብሮ (አቦ ሸማኔ አቦ) ወገቡስ የሱስ አይደል (አቦ ሸማኔ አቦ) አይበላም ወይ አብሮ (አቦ ሸማኔ አቦ) ልጁ የወይን ሀረግ (አቦ ሸማኔ አቦ) ጠይም አሳ መሳይ (አቦ ሸማኔ አቦ) እኔ እናቱን ብሆን (አቦ ሸማኔ አቦ) ለሰውም አላሳይ (አቦ ሸማኔ አቦ) (አቦ ሸማኔ አቦ) ሸማኔ አንተ ልጅ አንተ ልጅ አንተ ልጅ ያሙሃል ልብ ይበላል እንጂ አይሰጥም ይሉሃል በዚች በማተቤ እምልልሃለሁ ፍቅርህን ካልሰጠኸኝ እሞትብሃለሁ አሻፈረኝ እምቢ አትናገሩኝ ቅበሩኝ ገላችሁ የሰው ነው አትበሉኝ እኔስ ያንን ጀግና ተኝቼ አላልፈሙም ሀገር ጉድ ይበለኝ የኔ ነው የኔ ነው የኔ ነው የኔ ነው የኔ ነው የኔ ነው የኔ ነው የኔ ነው ደግሜ ደግሜ ደግሜ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out