Lyrics

ለእኛ የሚገባንን ጌታ ተቀበለ ለእኛ የሚገባንን ጌታ ተቀበለ ከመርገም ሊዋጀን በእንጨት ተሰቀለ ከመርገም ሊዋጀን በመስቀል ላይ ዋለ ከአሸናፊዎች ሊያስበልጠን ወዶ ሕያው አድርጎናል ሞታችንን ወስዶ አዲስ ኪዳን ገባን ታቅፈን በማዳኑ ሽንፈት የሌለበት የድል ነው ዘመኑ ለእኛ የሚገባንን ጌታ ተቀበለ ለእኛ የሚገባንን ጌታ ተቀበለ ከመርገም ሊዋጀን በእንጨት ተሰቀለ ከመርገም ሊዋጀን በመስቀል ላይ ዋለ ስለእኛ ተራቁቶ ማያረጅ ለብስ ሆነን ከእርሱ የተነሳ ታየን አሸብርቀን ተርቦ የሆነን የሕይወት እንጀራ እረፍትን ሰቶናል በመስቀሉ ስራ ለእኛ የሚገባንን ጌታ ተቀበለ ለእኛ የሚገባንን ጌታ ተቀበለ ከመርገም ሊዋጀን በእንጨት ተሰቀለ ከመርገም ሊዋጀን በመስቀል ላይ ዋለ ፍፁም በሆነ ፍቅር በሌለው ሽንገላ ተወደናልና ሌላውን አንጥላ ለሌላው ሰው መኖር ሲያስተምረን ጌታ አንዳች ሳይጎድልበት ለእኛ ተንገላታ ለእኛ የሚገባንን ጌታ ተቀበለ ለእኛ የሚገባንን ጌታ ተቀበለ ከመርገም ሊዋጀን በእንጨት ተሰቀለ ከመርገም ሊዋጀን በመስቀል ላይ ዋለ አንተ ይሆንክልን አይለካም በቃል ቢቀኝለት ዜማ ከዚህም ይልቃል ሕይወትህን ከፍለህ ህይወት ለሰጠሀን ሲነጋም ተመስገን ስመሽም ተመስገን ሕይወትህን ከፍለህ ህይወት ለሰጠሀን ሲነጋም ተመስገን ስመሽም ተመስገን ለእኛ የሚገባንን ጌታ ተቀበለ ለእኛ የሚገባንን ጌታ ተቀበለ ከመርገም ሊዋጀን በእንጨት ተሰቀለ ከመርገም ሊዋጀን በመስቀል ላይ ዋለ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out