Lyrics

ይፍረደኝ ተመልካች የሚያይሽ እንከን የለበትም ውበትሽ ቆንጆ ነሽ ነፍስ ነሽ (ቆንጆ ነሽ ነፍስ ነሽ) ይፍረደኝ ተመልካች የሚያይሽ እንከን የለበትም ውበትሽ ቆንጆ ነሽ ነፍስ ነሽ (ቆንጆ ነሽ ነፍስ ነሽ) አጃቢዋ ብዙ አድናቂ መች አጣች ፈርዶብኝ ነው መሰል በእኔ ላይ በረታች አምላክ ለሷ አድልቶ ውበትን ካደላት እኔ ደካማ ነኝ ታርገኝ ደስ እንዳላት ሁሌም ታምር መስራት አይደክመው ፈጣሪን (አይደክመው ፈጣሪን) ምን ያክል አልፈጀ አንቺ ስትሰሪ (አንቺ ስትሰሪ) ፀጉሯም ይሁንብት አይኗም ይሁንበ ጥርሷም ይሁንበት እንዴት ሰው ሲቆጣ ይጨምራል ውበት (ይጨምራል ውበት) ከግር እስከ ራሷ ሁሉንም ጨምሮ መቼ ታይቶ ያውቃል እንዲ ውብ ተፈጥሮ ይፍረደኝ ተመልካች የሚያይሽ እንከን የለበትም ውበትሽ ቆንጆ ነሽ ነፍስ ነሽ (ቆንጆ ነሽ ነፍስ ነሽ) ይፍረደኝ ተመልካች የሚያይሽ እንከን የለበትም ውበትሽ ቆንጆ ነሽ ነፍስ ነሽ (ቆንጆ ነሽ ነፍስ ነሽ) አይኔ ከምን ይደር ከየት ልመልሰው እንድህ እንከን አቶ ይፈጠራል ወይ ሰው እስኪ ተመልከቱት ውበቷን በሞቴ መውጣት ያምረኛል ወይ ብትገባ ከቤቴ እንደ መሳቅ ብላ አይኗን ስትገልጠው ያው እንደ ፈራሁት ልቤን አቀለጠው አይን አይኔን እያየች ብትሰጠኝ ፈገግታ የሰራ አካላቴ በፍቅሯ ተመታ ፍረዱብኝ በኔ አባይ ነው ብላቹ ድንቁን ተፈጥሮዋን ውበቷን አይታቹ ሁሌም ታምር መስራት አይደክመው ፈጣሪን (አይደክመው ፈጣሪን) ምን ያክል አልፈጀ አንቺ ስትሰሪ (አንቺ ስትሰሪ) ዳሌ ተረከዟ ባቷም ይሁንበት ሽንጧም ይሁንበት እንዴት ሰው ሲቆጣ ይጨምራል ውበት (ይጨምራል ውበት) ከግር እስከ ራሷ ሁሉንም ጨምሮ መቼ ታይቶ ያውቃል እንዲ ውብ ተፈጥሮ
Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out