Lyrics

ክርትት ባለ ውበት በዝምታ ቀልብን በሚስብ በመጠነ ፍካት በሰከነ አንደበት ተናግረሺኝ አንድ ያለኝ ልቤን አስከፈትሽኝ ፍስስ ባለ ውበት በዝምታ ቀልብን በሚስብ በመጠነ ፍካት በሰከነ አንደበት ተናግረሺኝ አንድ ያለኝ ልቤን አስከፈትሽኝ ውበትሽን አድንቄ ለመናገር አጣው ብዙ ቃላት ቢደረደር ክብርሽን ላወድስ ካሉት መሃል አነበብኩ ገልጬ ብዙ መፅሐፍ በሊቅ በጠቢባን ከተሳሉ አንድም አንቺን የለም የሚመስሉ ባጣ ከዚ ሁሉ ሚመስልሽ መልሶ አስደነቀኝ የማማርሽ ማር ማር ይላል ከንፈርሽ ስስት ልክ እንደስምሽ ማር ማር ደሞ አልሺኝና ቀረው ጣፈጥሺኝና ማር ማር ይላል ከንፈርሽ ለስለስ ልክ እንዳመልሽ ማር ማር ደሞ አልሺኝና ቀረው ጣፈጥሺኝና ክርትት ባለ ውበት በዝምታ ቀልብን በሚስብ በመጠነ ፍካት በሰከነ አንደበት ተናግረሺኝ አንድ ያለኝ ልቤን አስከፈትሽኝ ፍስስ ባለ ውበት በዝምታ ቀልብን በሚስብ በመጠነ ፍካት በሰከነ አንደበት ተናግረሺኝ አንድ ያለኝ ልቤን አስከፈትሽኝ ከፍጥረታት ሁሉ በምድር ላይ ለኔ አልተፈጠረም ካንቺም በላይ ፈጣሪስ በቃሉ ይሁን ካለው አብልጦሽ የለም ወይ ከፈጠረው በሊቅ በጠቢባን ከተሳሉ አንድም አንቺን የለም የሚመስሉ ባጣ ከዚ ሁሉ ሚመስልሽ መልሶ አስደነቀኝ የማማርሽ ማር ማር ይላል ከንፈርሽ ሰስቼ ልክ ስምሽ ማር ማር ደሞ አልሺኝና ቀረው ጣፈጥሺኝና ማር ማር ይላል ከንፈርሽ ለስለስ ልክ እንዳመልሽ ማር ማር ደሞ አልሺኝና ቀረው ጣፈጥሺኝና
Writer(s): Elias Woldemariam, Amanuel Yilma Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out