Featured In

Credits

PERFORMING ARTISTS
Lij Michael
Lij Michael
Performer
COMPOSITION & LYRICS
Lij Michael
Lij Michael
Songwriter

Lyrics

ናንዬ ናንዋ ወርቅ አልማዝ ገላዋ ከውቤ በርሀ ውለን ከአባ ኮራን እንደ ተኮላ ወርቅ ከሩቅ እያበራን እንዋደድ ነበር ሰው ነው ያፈራራን እንዋደድ ነበር ቀን ነው ያፈራራን ጣልያን አልጠገነው ባቡሩ ሰባራ አረማመድ አያውቅ የእኔ እግር ደንባራ አንቺን ጥሎበት ነው የተጋባው ግራ (ግራ ግራ) እንዴት ብትናፍቀኝ እንዴትስ ብትወደኝ እትቱ ስል አይታ ፍቅሯ እየበረደኝ ከሰው ለምዳ መጣች የባስ ልታነደኝ ሜሎቲ ቸኮላት ይዤ ባልሄድላት ነብሱን ይሰጥሻል አራዳ ነው በሏት ናንዬ (ናንዬ) ናንዋ (ናንዋ) ወርቅ አልማዝ (ወርቅ አልማዝ) ገላዋ (ገላዋ) ናንዬ (ናንዬ) ናንዋ (ናንዋ) ወርቅ አልማዝ (ወርቅ አልማዝ) ገላዋ (ገላዋ) ከውቤ በርሀ ውለን ከአባ ኮራን እንደ ተኮላ ወርቅ ከሩቅ እያበራን እንዋደድ ነበር ሰው ነው ያፈራራን እንዋደድ ነበር ቀን ነው ያፈራራን ጎበዝማ ነበር እንዴት ያለ አራዳ ሸርተት አረገና ጊዜም እንደከዳ የምቹ መድሃኒት ከደጅሽ እያለ አይቶ ማሳለፉን ልብሽ እንዴት ቻለ ሎሚ ተረከዝሽ መሬቱን ሲረግጠው የኔ ልብ ከወዲህ ምን አስደነገጠው እንደ አስናቀች ክራር ሳትደረደሪ ውይ ውይ ሳያስብልሽ ፍቅር እንደሜሪ ናንዬ (ናንዬ) ናንዋ (ናንዋ) ወርቅ አልማዝ (ወርቅ አልማዝ) ገላዋ (ገላዋ) ናንዬ (ናንዬ) ናንዋ (ናንዋ) ወርቅ አልማዝ (ወርቅ አልማዝ) ገላዋ ከውቤ በርሀ ውለን ከአባ ኮራን እንደ ተኮላ ወርቅ ከሩቅ እያበራን እንዋደድ ነበር ሰው ነው ያፈራራን እንዋደድ ነበር ቀን ነው ያፈራራን
Writer(s): Samuel Alemu, Lij Michael Lyrics powered by www.musixmatch.com
instagramSharePathic_arrow_out